የዘሩትን ማጨድ ለአፍታም ከማይለወጡ፣ ከማይዛነፉ የተፈጥሮ ህጎች አንዱ ነው፡፡

ብታውቀውም ባታውቀውም፣ ብታምነውም ባታምነውም በእያንዳንዷ የህይወትህ ቅጽበት የዘራኸውን ስታጭድ ኖረሃል፣ አሁንም እያጨድክ ነው፤ ውደፊትም እንዲሁ፡፡

ዋናው ልታደርገው የሚገባ ነገር ቢኖር ምን ዓይነት ዘር እየዘራህ እንዳለህ እና … ምን ዓይነት ፍሬ እያጨድክ እንዳለህ ቆም ብለህ ማገናዘብ ነው

ባደረከውም ግንዛቤ እያጨድክ ያለኸው ፍሬ ካላስደሰተህ፣ እየዘራህ የለውን ዘር በጥንቃቄ ምረጥ እና የምታጭደው ዘር በራሱ የምትፈልገው ዓይነት ሊሆን ግድ ነው፡፡



ለማሳ ያህል የሚከተሉትን ዝርዝሮች ተመልክት ንም ጤፍ ዘርቶ ስንዴ አይጠብቅም እና አንተም፡-

o  ጥላቻ ዘርተህ ፍቅር አትጠብቅም

o ስለበሽታ አስከፊነት ስታስብ እያዋልክ ጤናን አትጠብቅም

o ስለድህነት አስከፊነት እያሰብክ ሃብትን አትጠብቅም፣

o  ሰዎችን በሰሩትም ይሁን ባልሰሩት ጉዳይ ስታማ ውለህ አንተ ከሰዎች ምስጋና አትጠብቅም

o የመገናኛ ብዙኃን መረጃ ስትለቃቅም ውለህ የራስህ የሆነ አዲስ ሃሳብ እንዲኖርህ አትጠብቅም፣

 ዝርዝሩ የእተየለሌ ነው እና ተዘርዝሮ አያልቅም 

o ብቻ ላንተ የሚሆንህን ውሰድ እንዲሁም በዚህ ዝርዝር ያልተጠቀሱትን ጨምርበት ...


ልብ በል፡-

ሰው የዘራውን ያጭዳል ለሚለው ዋናው መሠረቱ ሁልጊዜም ቢሆን ሰው በተደጋጋሚ ያሰበውን ይሆናል ያገኛል እና በተደጋጋሚ የምታስባቸውን ሃሳቦች በጥንቃቄ ምረጥ!


አስተያየት ተጨማሪ ሃሳብ እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁ በዚሁ ድህረ-ገጽ ፃፉልን!