ስኬት ማለት ሰው በመጀመሪያ ማን መሆን፣ ምን ማግኘት እና ምን መስራት እንደሚፈልግ በንቁ አእምሮ በጥንቃቄ ማሰብ:: ይህንንም ሀሳብ ወደ ድብቁ አእምሮው በማስረጽ እምነት እና ስሜት በመገንባት መከፈል ያለበትን መስዋዕተነት በእያንዳንዱ ቅጽበት በደስታ እና በጉጉት መክፈል ነው፡፡ 

ይህም የሚሆነው ሰው በመጀመሪያ ማን መሆን፣ ምን ማግኘት እና ምን መስራት እንደሚፈልግ በንቁ አእምሮ በጥንቃቄ አስቦ በመወሰን፣ ይህንም ሀሳብ በተደጋጋሚ ቢያንስ በቀን ሰስት ጊዜ ማለትም ጠዋት ከእንቅልፉ እንደተነሳ፣ እኩለ ቀን ሲሆን እና ምሽት ከመተኛቱ ከ30 ደቂቃ በፊት ይህንን በተመስጦ ሆኖ መሆን፣ ማግኘት እና መስራት የፈለገውን ነገር አሁንኑ በተግባር ያገኘው ያህል ሲያምነው እና ስሜቱ ሲሰማው ነው፡፡ 

ይህንንም የእምነት እና የስሜት ግንባታ ለማፋጠን እና ለማጠንከር በእስኪብሪቶ ወረቀት ላይ በቀን ውስት የቻለውን ያህል ጊዜ በተደጋጋሚ መጻፍ ይችላል፡፡ ከዚህም የተወሰነ ቀናት ልምምድ በኋላ ሰውየው መሆን፣ ማግኘት እና መስራት የፈለገው ነገር በልቡ (በድብቁ አእምሮው ስለሚሰርጽ) በተጨባጭ የተከሰተ ያህል ሲያምነው እና ስሜቱ ሲሰማው ራሱን ያገኛል፡፡ በመቀጠልም ይህንን እምነት እና ስሜት በተግባር በገሃዱ ዓለም ለመግለጥ ዘና ብሎ እና በደስታ ተውጦ መከፈለ ያለበትን መስዋዕትነት ማለትም መሰራት ያለባቸውን ተግባራት አሁንኑ ያለምንም ድርድር ሲያደርግ ራሱን ያገኛል፡፡ ያኔ ይህ ሰው ስኬታማ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ለዚህም ነው ሰው በአእምሮው (በንቁ አእምሮው) በትኩረት ያሰበውን፤ በልቡ (በድብቁ አእምሮው) ያመነውን ማንኛውም ነገር ማግኘት ይችላል የሚባለው፡፡ ይህንን ሃሳብ ወደ ተግባር የሚቀይርብት መንገድ በማመቻቸት በህይወቱ ወደ ተግባር ያመጣ ማንኛውም ሰው ስኬታማ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህንን ሃሳብ ወደ ተግባር ከቀየረበት ቅጽበትም ጀምሮ ሰውየው ልክ የስኬት መፈብረኪያ ማሽን ያለው ያህል መሆን፣ ማግኘት እና መስራት የፈለገውን ማንኛውም ነገር ያለምንም ገደብ በተጨባጭ እና በተደጋጋሚ በማግኘት ከአንድ የስኬት ደረጃ ወደ ሌላ የስኬት ደረጃ እየተሸጋገረ ይኖራል፡፡ 

የስኬት መጨረሻ የለውምና ይልቁንም ስኬት ሁሌም መጨረሻ የሌለው የህይወት ጉዞ ሂደት ነው እንጅ፡፡ የፈለገውን ማንኛውም ነገር (ሃብት፣ ዝና፣ ጤና … ወዘተ) በማግኘት በዚህ ምድር በህይወት እስካለ ደረስ ደስተኛ እና ስኬት የተሞላበትን ህይወት መኖር ሲችል ይህ ሰው ስኬታማ ነው እንለዋለን፡፡ 

እጅግ በጣም ደስ የሚለው ዜና ደግሞ ይህንን ልምምድ ለማድረግ እና ጥበቡን ገንዘብ ለማድረግ ምንም ዓይነት ይትምህርት ደረጃ፣ ገንዘብ፣ ስልጣን፣ ዘመድ፣ ረጅም የዝግጅት ጊዜ… ወዘተ የማይፈልግ በነፃ የትኛውም የህይወት ደረጃ ላይ ያለ ሰው አሁንኑ ማድረግ የሚችለው መሆኑ ነው፡፡ 

ስለሆነም ውድ አንባቢየ ከዚህ የምትረዳው መሆን፣ ማግኘት እና መስራ የምትፈልገውን ነገር ለመሆን፣ ለማግኛት እና ለመስራት አንተ እንደምታስበው ይትምህርት ደረጃ፣ ገንዘብ፣ ስልጣን፣ ዘመድ፣ ረጅም የዝግጅት ጊዜ … ወዘተ አያስፈልገውም፡፡ ይልቁም አሁንኑ ካለህበት ሆነህ ማድረግ መጀመር ትችላለህ፡፡ 

የተግባር ሃሳብ፡-

ነገር ግን ይህንን ልምምድ ከመጀመርህ በፊት አንዳንድ ስለራስህ፣ ስለ አእምሮ አሰራር፣ ስለልማዶችህ፣ ስለ እምነቶችህ፣ ስለ ስዕብናህ፣ ስለስሜቶችህ እና ስለነገች ስላለህ አመለካከት በማጥናት እና በመረዳት ልታደርጋቸው የሚገቡ ቀዳሚ የቤት ስራዎች ይኖራሉ እና በቅድሚያ በተጠቀሱት የህይወት ዘርፎች መሰረት በመፈተሽ ስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይኖረርብሃል፡፡ በእርግጥም ራስን ማወቅ የስኬት መጀመሪያ ነውና::

 አንዴ ቆም ብለህ አስብ፡-

o ዛሬ አሁንኑ ልትተገብረው የምትችለው ከዚህ ጽሁፍ የተማርከው አንድ … ሁለት … ሶስት … ወዘተ ሃሳብ ምንድን ነው?  

o ስላንድ ነገር ብዙ መረጃ መኖር ዕውቀት ነው፤ መረጃውን በተግባር መጠቀም ደግሞ ጥበብ ነው እና አሁንኑ ዕውቀቱን በተግባር በመጠቀም አንድ እርምጃ ወደ ፊት 

በስተመጨረሻ ጥያቄ፣ አስተያየት፣ ተጨማሪ ሃሳብ ካለ በዚህ ድህረ-ገጽ ፃፉልን!