የስኬታማ ህይወት ጎዞህን
የምትጀምረው አሁንኑ ማን እንደሆንክ በማወቅ፣ ማን መሆን፣ ምን እንዲኖርህ እና ምን መስራ እንደምትፈልግ በጥልቅ በመገንዘብ
እና በመወሰን ነው፡፡ ስለዚህ አሁንኑ እስክብሪቶ እና ወረቀት በማዘጋጀት ራስህን ገምግመ፣ ማን መሆን፣ ምን እንዲኖርህ እና
ምን መስራ እንምተፈልግ በመወሰን ፃፋቸው፡፡
በመቀጠልም የአሁን ማንነትህን (ልማድህን፣ ስዕብናህን፣ ባህሪህን፣ አስተሳሰብህን፣ ስሜትህን) ወደ ምትፈልገው
አዲስ ማንነት የምትቀይርበትን መንገድ በማዘጋጀት በሂደት ቀይር::
የማትደራደርባቸውን የህይወት ዘርፎችህ (ጤና፣ ቤተሰብ፣ መንፈሳዊነት፣ ትምህርት …) በመምረጥ በእያንዳንዳቸው
በእነዚህ የህይወት ዘርፎችህ መቸ የት መድረስ እንደምትፈልግ ግብ አዘጋጅ::
በህይወትህ እንዲኖርህ እና መስራት የምትፈልገውን ነገር በጥንቃቄ በመለየት የምትፈልጋቸውን ነገሮች የምታገበኝበት ግልጽ ግብ ቅረጽ::
በስተመጨረሻም መላበስ የፈለከውን አዲስ ማንነት፣ የመረጥካቸውን የማትደራደርባቸውን የህይወት ዘርፎችን፣ በህይወትህ እንዲኖርህ እና መስራት የምትፈልጋቸውን ነገሮች ያሳኩ ከ3-5 ሰዎች በመምረጥ እና የእነዚህን ስኬታማ ሰዎች ሁሉ ነገራቸውን በጥንቃቄ በማጥናት ላንተ ሊጠቅምህ የሚችለውን በመውሰድ በየቅጽበቱ እና በየዕለቱ በራስህ ልምምድ ማደረግ ጀምር፡፡
ያኔ አንተ ከምታስበው በላይ ችልሎታህ እጅግ በጣም ጥልቅ እንደሆነ በመረዳት ስለራስህ
በመገረም የስኬት ጎዞን ትጀምራለህ፡፡
ጥያቄ፣ አስተያየት፣ ተጨማሪ ሃሳብ ካለ በዚህ ድህረ-ገጽ ፃፉልን!
0 አስተያየቶች