የስኬማ ህይወት ጉዞህን ዛሬ አሁንኑ በዚህ ቅጽበት እና እዚሁ መጀመር ትችላለህ፡፡ ብዙዎቻችን የስኬት ጉዟችንን አንድ ቀን እንደምንጀምር ለብዙ ጊዚያት እናስባለን፡፡ ምክንያቱም ዛሬ አሁንኑ በዚህ ቅጽበት ለስኬታማ ህይወት ጉዟችን መጀመሪያ የሚሆን ሊሰራ የሚችል አንዳች ነገር እንዳለ ዕውቀቱ ስለሌለን ነው፡፡
ዳሩ ግን የብዙዎችን ከፍተኛ የስኬታማ ህይወት ደረጃ የደረሱ ሰዎችን የህይወት ጎዞ ስንመረምር እነርሱም ልክ እንደእኛ ከዛሬው ህይወታቸው በፊት አንድ ቀን የስኬትን ህይወት ያልጀመሩበት ጊዜ ነበር፡፡ እናም ስለስኬት ቁጭ ብለው ሲያስቡ ነበር፡፡ በተለይ በተለይ ያኔ ኢነተርኔት ባልነበረበት ጊዜ ምንም የመነሻ ሃሳብ አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም ግን ከዕለታት ባንዲት ቀን ልክ እንደ እኛ ከምንም እና ከባዶ የስኬት ጉዟቸውን አሀዱ ብለው ጀመሩ፡፡ ይህንን ጽንሰ-ሃሳብ በሚገባ ትረዳው ዘንድ በአካል ባገኝህ ምን ያህል ጮሄ በነገርኩህ ነበር፡፡ ምክንያቱም ይህንን ልብ ካልክ አንድ ቀን ስኬታማ እሆናለሁ በማለት ተቀምጠህ ቀናትን፣ ሳንታትን፣ ወራትን እንዲሁም ዓመታትን ከመጠበቅ ይልቅ አሁንኑ ካለህበት ለስኬት ትነሳለህ፡፡
ስለሆነም እኛም አንድ ቀን እያልን የምንቀጥረው እና የምንናፍቀው ሌላ ጊዜ መኖር የለበትም፡፡ ሌላ የሚባል ጊዜ የለም፡፡ አትሞኝ! አትሸወድም! ትላንት ያለፈ እና ታሪክ የሆነ ዛሬ ነው፤ እንዲሁም ነገ ልንኖረው እንደምንችል እርግጠኛ ያልሆንበት ምዕናባዊ ዛሬ ነው፡፡ የፈለግነውን በእርግጠኝነት እና በተግባር ልንሰራበት የምትችለው ብቸኛው በእጃችን ያለ እውነተኛ ጊዜ አሁን ነውና ይልቁንም ራሳችንን ይህንን ጥያቄ በተደጋጋሚ እንጠይቅ፡- ''የስኬታማ ህወት ጉዞየን እውን ለማድረግ አሁን በዚህ ቅጽበት ምን ማድረግ እችላለሁ?''
ልብ ልንለውና ምንጊዜም መርሳት የሌለብን ዋና ነገር የሽ ኪሎሜትሮች ጉዞ በአንድ እርምጃ ነው የሚጀመረው፡፡ እሽ ይሁን ገብቶኛል፣ በጣም ደስ ብሎኛል፤ የስኬት ጉዞየን አሁን በዚህ ቅጽበት መጀመር እንዳለብኝም ተረዳሁ፣ አምኛለሁም፡፡ ታዲያ አሁን በዚህ ቅጽበት ምን ማድረግ እችላለሁ?
የስኬማ ህይወት ጉዞህን ዛሬ አሁንኑ መጀመር እንዳለብህ የሰጠውህን ማሰብ መጀመር እንደቤት ስራ ወስደህ ማሰብ ጀምር:: ይህንን ጽሁፍ በተደጋጋሚ በማንበብ የስኬት ጉዞህን ዛሬ አሁንኑ በዚህ ቅጽበት ጀምር እላለሁ፡፡
አንዴ ቆም ብለህ አስብ፡-
o ዛሬ አሁንኑ ልትተገብረው የምትችለው ከዚህ ጽሁፍ የተማርከው አንድ … ሁለት … ሶስት … ወዘተ ሃሳብ ምንድን ነው?
o ስላንድ ነገር ብዙ መረጃ መኖር ዕውቀት ነው፤ መረጃውን በተግባር መጠቀም ደግሞ ጥበብ ነው እና አሁንኑ ዕውቀቱን በተግባር በመጠቀም አንድ እርምጃ ወደ ፊት
በስተመጨረሻ
0 አስተያየቶች