የመነሻ ሃሳብ

ቂም ምን ያህል በራሳችን ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ብናውቅ በድለንም ብቻ ሳይሆን ተበድለንም ጭምር ይቅርታ ጠያቂ ራሳችን በሆ ነበር፡፡ ይቅርታ የሚያደርግ ምስጉን ነው:: መጥፎ ነገር ወይም ቂም በልብህ ለአንድ ቀን እንኳን አይደር፤ ፀሐይም ከመጥለቋ በፊት ይቅር በል ይላል የእግዚአብሔር ቃል:: 

ቂምን በውስጡ የያዘ ሰው  

የሞኝነት ሁሉ ጥግ ይቅርታን አለማድረግ ነው፤ በራሱ አእምሮ ላይ አመጽን ቀስቅሷልና። ልብ በሉ በአእምሯችን ቂም (የክፉ ነገር ዕቅድን) ስንይዝ በመጀመሪያ ቂሙን የፈጠርነው፣ ቀጥሎም የያዝነው፣ የተሸከምነው በራሳችን አእምሮ ነው። በመሆኑም ይህን መጥፎ ነገር ዕቅድ ወይም ቂም በራሳችን አእምሮ እናመላልሳለን። በጣም የሚገርመው በአእምሯችን የያዝነው ይህ መጥፎ ነገር (ቂም) የተያዘበትን ሰው ብቻ ሳይሆን በቂም ያዡ ሰው ዙሪያ ያሉ ሌሎች ሰዎችና ውሃን ሳይቀር ያውካል፣ ይበክላል። አስቡት ይህ ከሆነ መጥፎ ነገሩን ወይም ቂን በአእምሮው የያዘው ሰው እንዴት ሊጎዳ እንደሚችል መገመት ቀላል ነው።

ጉዳቱም ከአእምሯዊ ጉዳት በዘለለ ከፍተኛ አካላዊ ጉዳት አለዉ። ቆዳችን ክፉኛ ይቀላል፣ ይገረጣል:: ወና ዋና የአከካል ክፍሎቻችን (ልብ፣ ኩላለሊት፣ አእምሮ፣ ሳንባ …) በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳሉ፡፡ እንዲሁም አይኖቻችን ክፉኛ ይቀላሉ፣ አጠቃላይ ጡንቻዎቻችን የአእምሮ ጡንቻዎችን ጨምሮ በመጥፎ ነገሩ ወይም ይቀቀላሉ፣ ይበስሉማል፣ የምግብ ፍላጎታችን ይቀንሳል። ከዚህና ከሌሎች ካልተጠቀሱት ችግሮች የተነሳ አሉ የተባሉ መጥፎ ክስተቶች ማጠራቀሚያ እንሆናል፡፡ ሰዉ የዘራውን ያጭዳልና በስመጨረሻም ዕደሚያችንን በራሳችን ፍላጎት እንቀንሳለን፣ አሉ ተባሉ ከበባድ በሽታዎች ክፉኛ ስለምንጎዳ

ዕድሚያችንን በራሳችን ማሳጠራችን እንኳን ቢቀር እና በምድር ላይ የሽ ዓመታት የመኖር ጸጋ ቢሰጠ እንዲያውም እንደ ቅድመ አያቶቻችን አዳምና ሄዋን ኤደን ገነት መኖሪያችን ሆና ብትሰጠ እንኳን በህይወታችንደሰትም። ምክንቱም ቀድሞ ነገር የእኛ ችግር የዕድሜና የመኖሪያ ቦታ እጥረት አይደለ  ይልንም የእኛ መሠረታዊ ችግር ይር ማለት ስንችል በራሳችን አእምሮ መጥፎ ነገር ዕቅድን ወይም ቂምን በመሸከም በራሳችን ላይ አመፅን ማስነሳታችን ነው እንጅ::

ለምሳሌ ዛፋ የተጎዳው ስሩ ላይ ከሆነ ግንዱን፣ ቅርንጫፉን፣ ቅጠሉን እና አበባውን ብናክመው ምን ይጠቅመዋል? ታዲያ እኛም ቂመኞች የተጎዳነው በራሳችን አእምሮ ውስጥ የመጥፎ ነገርን ዕቅድ (ቂም) በመያዛችን ሆኖ ሳለ ረጅም ዕድሜ እና ምቹ የሞኖሪያ ቦታ ቢሰጠን ምን ይጠቅመናል፡፡ ቀድሞ ነገር ባለችን ዕድሜ እና ባለንበት የመኖሪያ ቦታ በይቅርታ መኖር ተስኖን ሳለ ረጅም ዕድሜ እና ምቹ የሞኖሪያ ቦታ እንዴት እንዴትስ እንሰጣለን፡፡ በትንሹ የታመነ በትልቁ ይሾማል አይደል የሚባለው፡፡ ደግሞስ ይቅርታን የማያውቅ አመጸኛ ሰዉ በሰላሙ ከተማ ውስጥ ሆኖ በራሱ በውስጡ አመፅ ይስቃያል፤ ሰላማዊ እና ይቅር ባይና ሰው ደግሞ በአመፅ ከተማ ዉስጥ ሆኖ በውስጡ በአእምሮው ሰላም በአምላኩ ደስ ብሎት ይኖራል አይደል ነገሩ

ልብ እንበል አንድ ሰው በአእምሮው በአንድ ጊዜ ሁለት ነገርን መሆን አይችልም። በመሆኑም መጥፎ ነገርን ወይም ቂምን ይዞ በአእምሮ ሰላም መሆን የማይታሰብ ነው። የሚኖርበት ከተማ ምንም ያህል ሰላም ቢሆንም በውሰጡ ይታወካል፡፡ እንዲሁም ውሰጡ ሰላምን የያዘ ሰው የሚኖርበት ከተማ ምንምህል ቢረበሽም በውሰጡ ሰላም ነው፡፡ ቀድሞ ነገርም የደግ ሰው የሰላም ምንጩ የዓለም ነገር ሳይሆን የእግዚአብሔር ነውና፡፡

ቂም ተያዘበት ሰው

ቂም የተያዘበትም ሰው ቢሆን ሰህተተኛ ሊሆን ይችላል። ሰው ቀድሞውኑ ሰው እንጂ መልአክ አይደለም፡፡ በማወቅም ባለማወቅም ስህተት እና በደልን እንደሚያደርግ በእግዚአብሄርም የታወቀ ነገር ነው። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በሰራው መጥፎ ነገር በመጸጸት ይቅርታን መጠየቅ አለበት:: ለሰዎች መከፋት መንስኤ ሆኗልና። ይህንንም በተረዳ ቅበት ይቅርታን ካልጠየቀ በደለኛ ነው። ይህንን ካደረገ ግን ከስህተትና ከበደሉ ይነፃል፡፡

ስለሆነም የተበደለው ሰዉ የበደል መጠን ምንም ይሁን ምን፤ ይቅር ይበልም አይበልም ሰህተትና በደሉን የሰራው ሰው በእውኑ ይቅር ካለ አንድም አምላኩ ይቅር ይለዋል። አንድም ራሱ ከያዘው የመጥፎ ነገር ዕቅድ (ቂም) የውስጥ ቅጣት ነ ይወጣል፡፡ የተባዳዩን ይቅርታ የማለት ልብ የማሸነፍ ሙሉ ስልጣን የለውምና። ደግሞም ተበዳይ ልብ ቢል በእውኑ ይቅር የማይባል ሰህተትና በደል አለ? አምላኩ ያለጥፋቱ በቀራንዮ አደባባይ በመስቀል ላይ የሰቀሉትን እንኳን ሳይቀር አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁም እና ይቅር በላቸው በማለት ምንም ይቅር የማይባል ስህተት እና በደል የሌለ መሆኑን ልብ ሊል ይገባው ነበር፡፡ ከዚህ ሁሉ ዝርዝር ውጭ በሆነ መንገድ ተበዳይም ሆነ በዳይ ወይም ከሁለት አንዱ በትዕቢት ወደ ቤ ቢመላለሱ በእውኑ ምን ይጠቅማቸዋል? በፍሪያቸው ታውቋቸዋላችሁ በተባሉ ጊዜ መልሱ አናውቃቸውም ነውና።

ለመሆኑ ሰዉ እንደዚህ አይነቱን ነገር (ከይቅርታ ይልቅ ትዕቢትን) ከየትስ ተማረው?

እዚህ ላይ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አዳም እና ሄዋን ለመጀመሪያ ጊዜ ተንኮልን፣ ትዕቢትን፣ ቂምን  እንዴት እና ከማን እንደተማሩት ላወሳ አልወደድኩም፡፡ ይህ በሁላችንም የታወቀ እና ለብዙዎቻች የተንኮል፣ የትዕቢት፣ የቂም ህይወት የነበረ አሁን ግን ያለፈ ነውና፡፡ ላወራ የፈለኩት እነዴት ከትውልደ ወደ ትውልድ እንደተላለፈ ነው፡፡

በመጀመሪያ ያኔ በደመነፍሳዊ ማንነቱ በነበረ ጊዜ በቅርቡ ከነበረው ሰው (ከእናትና ከአባቱ፣ ከአሳዳጊው አና ከሌሎች ቅርብ ቤተሰብ አባላት) በተደጋጋሚ በማየትና በመስማት ነው የተማረው። ለዚህ ነው ልጆች የወላጆች ወይም የአሳዳጊዎች ነጸብራቅ ናቸው የሚባለው። እዚህ ላይ መታወቅ ለበት በጣም አደገኛው ነገር ደግሞ ይህ የተበዳይና የበዳይ በቂም በተግባር የተገለጠ ህይወት ከትውልድ ወደ ትውልድ ማለትም ወደ ልጆች በመተላለፍ ዘላቂ የህይወት አደጋ ይሆናል። እንደ ሃገር በኢትዮጵያ፣ ግለሰብ በየቤቶቻችን ከጎረቤት እና ከቤተሰቦቻችን ዛሬውኑ አሁን በዚህ ቅጽበት ሳይቀር እየሆነ ያለው ይህ ነው፡፡ 

ለመሆኑ ለዚህ ይቅርታ-አልባ ህይወት መፍትሄ ምን ይሆን?

ደስ የሚለው ነገር እግዚአብሄር የስህተትንና የበደልን መስራት እንዲሁም የስህተትንና የበደልን መጠን የሚመዝን አይደለም::  ይቅርታ የሚጠይቅን እና የሚያደርግን ልብ ብቻ የሚሻ አምላክ ነው። ለእኛ በእያንዳንዱ ቅጽበት እና ቀን በስህተት እና በበደል ውቅያኖስ ውስጥ ተዘፍቀን ለምንኖር ከዚህ በላይ የተስፋ ቃል እና መጽናኛ ም አለ? 

ስለተደረገብን ሳይሆን ስለተደረገልን እናስተውል!!!


ተጨማሪ ሃሳብ፣ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ ፃፉልን!