የመነሻ ሃሳብ

እያንዳንዱ የህይወት ዘርፎቻችን በህይወታችን በተግባር የሚገለጡት በቀን ውሏችን ነው፡፡ እንዲሁም አንድ ሰው ምንም ያህል ረጅም ዓመታትን የሚወስድ ትልቅ የህይወት ዓላማ ቢኖረው ወርዶ ወርዶ ዓላማው መሬት ላይ የሚኖረው በባለዓላማው ሰው በእያንዳንዷ የቀን ውሎው ነው፡፡ በውሏችን መሰረት እያንዳንዷ ቀን ወደ ዓላችን ታስጠጋናለች ወይም ከዓላማችን ታርቀናለች፡፡ ስለሆነም ቀናችንን በጥንቃቄ ማቀድ እና ባቀድነው መሰረት መዋል መለማመድ ለሁላችንም ይደር የማይባል ቀዳሚ ተግባራችን ሊሆን ይገባል፡፡

ጠዋት የመነሳት ጥቅ

ጠዋት የመነሳት ዋናው ጥቅሙ እጅግ በጣም ጥርት ያለ እና ከረብሻ ነፃ የሆነ ትርፍ ጊዜን እናገኛለን፡፡ በህይወታቸው ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ጠዋት ሁላችንም በተኛንበት ምንም ዓይነት የሚረብሻቸው ነገር በሌለበት ተtነስተው በዓለም ላይ ሊያመጡት ስለሚችሉት እሴት ጠንክረው ያስባሉ፡፡ በዚህም ልማዳቸው ከ24 ሰዓታት በላይ ያላቸው እስኪመስል ድረስ ከዓለም ህዝብ ሁሉ ከፍ ብለው ይታያሉ፡፡ እኛስ በእውኑ ይህንን እንዳናርግ ያገደን ምንድን ነው? መነሳት እና ጥር ያለ ከእረብሻ ነፃ የሆነ ሰዓት በማግኘት ልናሻሽለው በምንፈልገው የህይወት ዘርፋችን ማሰብ፣ ቀናችንን ማቀድ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት ቀናችንን በደስታ መጀመር እንችላለን፡፡

ጠዋት በቀንህ መጀመሪያ ስንት ሰዓት ትነሳለህ፣ ምንስ ታስባለህ?

የሰው ልጅ የቀን ውሎው ገና ከጠዋቱ ይጀመራል፡፡ ቀናችንን በስንት ሰዓት እና በምን አይነት ስነ-ልቦና ወይም ሃሳብ ነው የምንቀበለው የሚለው የአንድ ሰው የህይወት ስኬት ወይም ውድቀት ዋና መለኪያ መስፈርት ነው፡፡ መደበኛ ሰው ቀኑን አርፍዶ ይጀምራል:: ይባስም ብሎ የሚያናድደውን፣ የሚያሳዝነውን ባጠቃላይም ደስ የማይለውን የትናንት ዜና፣ ሰው፣ ክስተት፣ የቀን ውሎ፣ ጥፋቱንወዘተ በማሰብ፡፡ ብዙዎቻችን ጠዋት መነሳት ተራራ የመውጣት ያህል ይከብደናል፡፡ ይህ ማለት ግን ጠዋት መነሳት ከባድ ነው ማለት አይደለም ልማዳችን አርፍዶ መነሳት ስላልሆነ እንጅ፡፡

ስለሆነም ጠዋት መነሳት ከፈለግን አርፍዶ የመነሳት ልማዳችንን ጠዋት በመነሳት መተካት ነው፡፡ ጠዋት የመነሳት ልማድን ለማዳበር የተለያዩ ዘዴዎችን መጠቀም ይቻላል፡፡ የምንተኛበትን ሰዓት አስበን መወሰን እና በተቻለ መጠን መደበኛ ማድረግ፣ ማንቂያ ደወል በመቅጠር ከተኛንበት ራቅ እድርገን ማስቀመጥ ሲጮህ ለማጥፋትም ቢሆን እንድንነሳ፡፡ እንዲሁም የሚቀሰቅሰን የቤተሰብ አባል ወይም ሌላ ሰው በስልክ እንዲቀሰቅሰን ቀጠሮ መያዝ፡፡ ይህን ጠዋት የመነሳትም ሆነ ማንኛውም ልምምድ ልማድ ለማድረግ ቢበዛ ሶስት ሳምንት ነው የምንቸገረው፡፡ ከዚያ በኋላ ለእንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የህይወታችን አንድ አካል ይሆናል፡፡

ጠዋት እንደተነሳህ ምን ታስባለህ፣ ምንስ ትሰራለህ?

መደበኛ ሰው ቀኑን አርፍዶ መጀመሩ ሳያንሰው ከምኝታው እንደተነሳ የሚያስበው፣ የሚያየው እና የሚሰማው የሚያናድደውን፣ የሚያሳዝነውን ባጠቃላይም ደስ የማይለውን የትናንት ዜና፣ ሰው፣ ክስተት፣ የቀን ውሎ፣ ጥፋቱንወዘተ ነው፡፡ ገና ከጠዋቱ አእምሮውን የሚያናድደውንና የሚያሳዝነውን የትናንት ዜና፣ ሰው፣ ክስተት፣ የቀን ውሎ፣ ጥፋቱንወዘተ ስለሚመግበው ሳያውቀው ሙሉ ቀኑን ምንም ዓይነት ስራ ላይም ሆኖ ሳለ ያንን ሲያስብ ይውላል፡፡ እንያውም በቀን ውሎው የሚያሳዝነውና የሚያናድደው ነገር ይገጥመዋል፡፡

በዚህ መልኩ ቀኑ ይጠናቀቅ እና ቤቱ ሲመለስም የአእምሮው የቀን ውሎ ትኩርት በሚያሳዝን እና በሚያናድደ ነገር ላይ ስለነበር ከቤቱም እንዲሁ የሚያሳዝን እና በሚያናድድ ነገርን ይፈልግለታል፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት የህይወት ዑደት ላይ ያለን ሰዎች መሰረታዊው ችግራችን አእምሯችን እኛን ይጠቀምብናል እንጅ እኛ አእምሯችን አንጠቀምበትም፡፡ ስለ አእምሯችን አጠቃቀም የበለጠ ግንዛቤ ለማግኘት ከዚህ በፊት በዚህ ድህረ-ገጽ አእምሮን መጠቀም አሁንኑ ተጫንና በጥንቃቄ አንብበው፡፡

በዚህም የተነሳ በህይወታችን በሚሆኑብን ነገሮች ላይ ሃላፊነቱን ወስደን ከማስተካከል ይልቅ ከአቅማችን በላይ ስለሚመስለን እንዲሁ በሆነብን ነገር እያዘንንና እየተናደድን እንኖራለን፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ጠዋት እንደተነሳህ የምታስባቸውን ነገሮች ሆን ብለህ በመምረት እነሱ ላይ ማተኮር ልማድህ እስኪህ ድረስ ተለማመድ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ደግሞ ሊያሳዝኑህ እና ሊያናድዱህ ከሚችሉ ነገሮች ራቅ፡፡ እኔ ጠዋት እንደተነሳሁ ሁሌም ማሻሻል በምፈልገው የህይወት ዘርፌ በተመለከተ መጽሐፍ በማንበብ እና ስፖር በመስራት ነው ቀኔን የምጀምረው፡፡

ከመተኛትህ በፊት ምን ታስባለህ፣ ምንስ ትሰራለህ፣ ስንት ሰዓት ትተኛለህ?

እኒህ ጥያቄዎች ከላይ ከላይ ስታዩ ቀላል እና ግልጽ ቢመስሉም ለህይወት ስኬታች ግን እጅግ በጣም ወሳኝ የመሰረት ድንጋዮች ናቸው፡፡ መቸም ቀናችንን በዋልነው ሁሉ ውለን መተኛታችን አይቀሬ ነውና ከላይ የሉትን ጥያቄዎች በጥንቃቄ መመለስ አለብን፡፡ የሰው ልጅ ሲተኛ ይዞት የተኛውን ሃሳብ እና ስሜት ጠዋት ሲነሳ የህይወቱ አካል ሆኖ ያገኘዋል፡፡ ስለዚህ የሚያናድድህን እና የሚያሳዝንህን ዜና፣ ሰው፣ ክስተት ... ወዘተ እያሰብክ ብትተኛ ጠዋት ስትነሳ ህይወትህ ምን እንደሚመስል አስበው፡፡ ለዚህም ምናልባት ከዚህ በፊት በዚህ ድህረ-ገጽ በህይወታችን ስኬታማ ለመሆን እንደ ህፃናት እንሁን አሁንኑ ተጫንና በጥንቃቄ አንብበው:: አንባቢዎች ላነሱት የተጨማሪ መረጃ ጥያቄ መሰረት የሰጠነው ምላሽ ነው፡፡ ምሽት የምንተኛበት ሰዓት እና እያሰብ የምንተኛው ሃሳብ የቀና ብሎም የህይወ አቅጣጫ የመቀየር አቅም አላቸውና ከዛሬ ጀምሮ ልብ እንበል፡፡ እኔ በበኩሌ ልተኛ ስል ከምሰራቸው ስራዎች በሚቀጥለው ቀን ምን እንደምሰራ መወሰን እና መቀድ ነው፡፡

ማጠቃለያ

@ ህይወታችንን በተግባር የምንኖርበት ተጨባጩ ሁኔታ የቀን ውሎ ነው፡፡
@ ሰው ምንም ትልቅ ዓላማ ቢኖረው ዓላማው የሚገለጠው በቀን ውሎው ነው፡፡
@ የቀን ውሏችን ወደ ዓላማችን ታስጠጋናለች ወይም ከዓላማችን ታርቀናለች፡፡
@ ስለሆነም ቀናችንን በጥንቃቄ ማቀድ እና ባቀድነው መዋል ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
@ ስንቶቻችን ባቀድነው መሰረት ቀን እንውላለን? 

አንዴ ቆም ብለህ አስብ፡-

ዛሬ አሁንኑ ልትተገብረው የምትችለው ከዚህ ጽሁፍ የተማርከው አንድ … ሁለት … ሶስት … ወዘተ ሃሳብ ምንድን ነው?  

ስላንድ ነገር ብዙ መረጃ መኖር ዕውቀት ነው፤ መረጃውን በተግባር መጠቀም ደግሞ ጥበብ ነው እና አሁንኑ በተግባር ግባ!

 

አስተያየት ተጨማሪ ሃሳብ እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁ በዚሁ ድህረ-ገጽ ፃፉልን!