መነሻ ሃሳብ

ጠባቡ መንገድ ምንጊዜም ፈታኝ ነው፡፡ ነገር ግን ምንጊዜም አዋጭ እና አትራፊ ነው፡፡ ጊዚያዊ ምቾትን ያሳጣል፣ ጊዚያዊ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ደስ የሚለው ግን ዘላቂ ምቾትን እና ትሩፋትን ያስገኛል፡፡ ሰፊው መንገድ ምንጊዜም ቀላል ነው፡፡ ነገር ግን ውጤቱ ውድቀት እና አክሳሪ፡፡ ጊዚያዊ ደስታን ይሰጣል፣ ዘላቂ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ፈጣሪ ራሱ ጠባቡን መንገድ ተከተሉ ያለው ለዚሁ ነው፡፡

ሰፊው መንገድ

የሰው መሰረታዊ ችግር በሰፊው መንገድ በመሄድ ጊዚያዊ ደስታን እና ተቀባይነትን በሌሎች ዘንድ በማግኘት መመሳሰል እና በዘላቂነት መውድቅ ነው፡፡ ስለሆነም ከብዙዎች ሰዎች በብዙ መንገድ የተለየ የሆነ (ጠባቡን መንገድ) የተከተለ ሰው በህይወቱ ስኬታማ ነው፡፡ ምንያቱም ብዙ ሰው የሚከተለው ተመሳይ የሆነውን (ሰፊውን) የውድቀት መንገድ ነው፡፡ ራስን መሆን ውበት ነው የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡ እያንዳንዳች ራሳችንን ብንሆን ማንም ሰው የሌለውን ማንነት ስለምናንጸባርቅ ለሰው ልጆች ሸክም እና እዳ ከመሆን ይልቅ በረከት እና ትሩፋት እንሆናለን፡፡ ልዩነታችን ውበታችን ነው የሚባለውም ለዚሁ ነው፡፡

በዚህ ጽሁፍ ሰፊው መንገድ ብየ የጠቀስኳቸው መንፈሳዊውን ብቻ ሳይሆን ዓለማዊውን ህይወታችንም የሚገልጹ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት ሰፊው መንገድ የተባሉት በዓለም አቀፍ ደረጅ ከ98% በላይ የሆነው ህዝብ በተመሳይ ሁኔታ በቀን ውሎው የሚያደርጋቸው ናቸው፡፡ እነሱም ተኝቶ ማርፈድ፣ አለማንበብ፣ አለመፃፍ፣ መዋሸት፣ ሰዎችን ማማት፣ ማማረር፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለመስራት፣ አሉታዊ ሃሳብ ማሰብ፣ ቂም መያዝ፣ መናደድ፣ ማዘን፣ እምነተ-ቢስ መሆን፣ ዓላማ-ቢስ መሆን ጨምሩበትና ወዘተ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እኒህ እና መሰል ነገሮች ሰፊው መንገድ ተብለው የተጠሩት የብዙዎቻን የቀን ተቀን የህይወት እውነታዎች ናቸው፡፡

ጠባቡ መንገድ 

በዚህ ጽሁፍ ሰፊው መንገድ ብየ የጠቀስኳቸው መንፈሳዊውን ብቻ ሳይሆን ዓለማዊውን ህይወታችንም የሚገልጹ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት ጠባቡ መንገድ የተባሉት ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ2% በታች የሆኑት ሰዎች የሚከተሉት ሲሆን የሰፊው መንገድ ግልባጮች ናቸው፡፡ እነሱም በጠዋት መነሳት፣ በመደበኛ መል ማንበብ እና መፃፍ፣ ሃቀኝነት፣ ማመስገን፣ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት፣ አዎንታዊ እና ቅን ሃሳቦችን ብቻ ማሰብ፣ ይቅርታ ማድረግ፣ ደስተኛ መሆን፣ ተስፈኝነት፣ አማኝ፣ ባለራዕይ መሆን ወዘተ ጨምሩበትና ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ልዩ መሆን በአግባቡ መረዳት

ልዩ መሆን ማለት እንዲሁ በግብዝነት ከሰዎች ለመለየት ተብሎ ብቻ የምንሆነው ሳይሆን ብዙ ሰዎች የማያደርጉት ግን መሆን ያለበትን ነገር በልዩነት ማድረግ እና መሆን ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ብዙ ሰው ሰዎች ካላወቁበት መዋሸት እና ማስመሰል የተለመደ ሰፊ መንገድ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ጠባን መንገድ የሚከተል እና ልዩ የሆነ ሰው ዎች ቢያዩትም ባያዩትም ለራሱ እና ለሰዎች ታማኝ መሆን ማለት ነው፡፡  

ይሁን እንጅ አንዳንድ ጊዜ ልዩ መሆንን በቅንጭቡ በመረዳት ልዩ ለመሆን ብቻ ሲሉ ብዙ ሰዎች ያልሆነ ነገርን ሲሆኑ ይታያል፡፡ ለምሳሌ ግልጽ በሆኑ እውነታዎች ላይ ሳይቀር የሙጥ ብሎ ተቃራኒ ሃሳብ ማቅረብና መከራከር፣ ከተለመዱ እና ጠቃሚ ከሆኑ ልማዶች አለባበሶች ማፈንገጥ፣ ለላፊ፣ ለታላቅ አለመታዘዝ ወዘተ ናቸው፡፡

ጠባቡን መንገድ የመከተል ፈተናዎች

ብዙ ሰዎች ይህንን ጠባቡን መንገድ የመከተል አማራጭ ስታቀርብላቸው በዚህ ዘመን እና በዚህ ሃገር ጠባን መንገድ መከተል የማይታሰብ ነው ይሉል፡፡ በዚህ መንገድ ከሄድክም መኖር እንደማትችል ምሳሌዎች በማድረግ ይነግሩሃል፡፡ እርግጥ ነው በውሸታሞች ሰፈር እውነተኛ ሆኖ ለመኖር ፈታኝ ነው፡፡ ጠባቡን እና የእውነተኛውን መንገድ ይዘን ስኖር ሳለን ብዙዎች ይሞግናል፣ ብሎም ዋጋም ያስከፍከለናል፡፡ መረሳት የሌለበት ግን ሰፊውን መንገድ መከተልም እንዲሁ የበለጠ ዋጋ እያስከፈለን መሆኑን ነው፡፡ 

ሌላው ልብ ልንለው የሚገባው ነገር ደግሞ ጠባቡን መንገድ መከተል የህይወት ልምምዳችን ለማድረግ ሌሎች ከሚያደርሱብን ተጽዕኖ የበለጠ እውነተኛው እና ትልቁ ፈተናችን የሚሆነው ሰፊውን መንገድ መከተል የህይወት ልምዱ ያልሆነው የራሳችን ማንነት ነው፡፡ ስለዚህ ጠባን መንገድ በመከተል ልምምድ ላይ ትኩረት ማድረግ እና ብዙ ጊዜ እና ጉልበት መመደብ ያለብን በየዕለቱ ራሳችንን ማሰልጠን ላይ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሌላው ብዙዎቻን የምንረሳው አንድ ሃቅ ጠባቡን መንገድ ስንከተል ፈጣሪያችን ከጎናችን ሆኖ እንደሚረዳን ነው፡፡ እውነት ያድናችኋል እና እውነትን ተከተሉ የሚለውን አምላካዊ ኃይለ-ቃል ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡

ብዙዎቻችን በዕድገታችን ሂደት ሌሎችን በማየት ስላደግን በመንጋ መነዳት እና መመሳሰል የህይወታችን መርቸህ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ጠባቡን መንገድ የመከተል አማራጭ ሲቀርብልን በዚህ ዘመን እና በዚህ ሃገር ጠባቡንመንገድ መከተል የማይታሰብ ይሆንብናል፡፡ በዚህ መንገድ ከሄድንም መኖር እንደማንችል እናስባለን እናምናለንም፡፡ እርግጥ ነው በውሸታሞች ሰፈር እውነተኛ ሆኖ ለመኖር ፈታኝ ነው፡፡ በሰነፎችም መንደር ታታሪ ሆኖ መኖር ፈታኝ ነው፡፡ ጠባቡን እና የእውነተኛውን መንገድ ይዘን ስብኖር ሳለን ብዙዎች ይሞግቱናል፣ ምናልባትም ጊዚያዊ ዋጋም ያስከፍከለናል፡፡ መረሳት የሌለበት ግን ሰፊውን መንገድ መከተልም እንዲያውም ዘላቂ ዋጋን እያስከፈለን ነው፡፡ 

አንድ ልብ ልንለው የሚገባው ነገር ደግሞ ጠባቡን መንገድ መከተል የህይወት ልምምዳችን ለማድረግ ሌሎች ከሚያደርሱብን ተጽዕኖ የበለጠ እውነተኛው እና ትልቁ ፈተናችን የሚሆነው ሰፊውን መንገድ መከተል የህይወት ልምምዱ አድርጎ የኖረው የራሳችን ማንነት ነው፡፡ 

ስለሆነም ጠባን መንገድ በመከተል ልምምድ ላይ ትኩረት ማድረግ እና ብዙ ጊዜ እና ጉልበት መመደብ ያለብን በየዕለቱ ራሳችንን ማሰልጠን ላይ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሌላው ብዙዎቻን የምንረሳው አንድ ሃቅ ጠባቡን መንገድ ስንከተል ፈጣሪያችን ከጎናችን ሆኖ እንደሚረዳን ነው፡፡ እውነት ያድናችኋል እና እውነትን ተከተሉ የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡

ጠባቡን መንገድ የመከተል ልምምድ 

አሁን መመለስ ያለበት ትልቁ የእያንዳንዳችን ጥያቄ እኛ በብዙ ህይወታችን የትኛውን መንገድ እየተከተልን ነው የሚለው ነው፡፡ ጠባቡን ወይስ ሰፊውን መንገድ? እስካሁን በነበረው ህይወታችን የትኛውንም መንገድ ብንከተል ችግር የለውም፡፡ ዋናው ነገር በትክክል የትኛውን እየከተልን እንደሆነ መገንዘቡ ነው፡፡ በመቀጠልም የየዕለት ልምምዳችንን ጠባቡን መንገድ መከተልን ማድረግ ነው፡፡ ማንም ሰው ይህንን ጠባብ እና ሰፊ መንገድ ምንነት በሚገባ በመረዳት፣ በህይወቱ ጠባቡን መንገድ የመከተል ልምምድ ቢያደርግ በህይወቱ ስኬታማ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ጠባብ መንገድ መከተል ልማዱ ያደረገ ማንነትን ለመፍጠር ራስን ማሰልጠን የየዕለት ትኩረታችን ሊሆን ይገባል፡፡

የቤት ስራ

አሁንኑ ይህንን ጽሁፍ አንብበህ እንደጨረስክ ዛሬ ከዚህ ቅጽበት ጀምሮ በህይወትህ ልምምድህ ብታደርጋቸው የምትወዳቸውን ጠባብ መንገዶች በደብተርህ ላይ ፃፍ፡፡ ከእነዚህም መካከል ለዚህ ሳምንት ሶስቱን ለራስ በመታመን መለማመድ ጀምር፡፡ ልብ በል ማወቅ የህይወት ስኬት ጅማሮ ነው፡፡ ያወቁትን ወዲያውኑ መተግበር መጀመር ደግሞ በጥበብ መኖር ነው እና አሁንኑ ወስን፣ በጠባቡ መንገድ መኖርንም ጀምር፡፡

ጥያቄዎች

እስኪ እናንተ የምትከተሏቸውን ሰፊው መንገዶች ፃፉልን

----------------------------------------------------------------------

----------------------------------------------------------------------

----------------------------------------------------------------------

 

ልትለማመዷቸው የወሰናችኋቸው ጠባብ መንገድስ እነማን ናቸው?

----------------------------------------------------------------------

----------------------------------------------------------------------

----------------------------------------------------------------------

በዚህ ሳምንት ልትለማመዷቸው የወሰናችኋቸው ሶስቱ ጠባብ መንገዶች እነማን ናቸው?

----------------------------------------------------------------------

----------------------------------------------------------------------

----------------------------------------------------------------------

በጽሁ ላይ ተጨማሪ ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ጥያቄ ካለ መነጋገር መርሃችን ነው፡፡

ጽሁፉ ይጠቅማል ብለው ካሰቡ ለሌሎች ያጋሩ፡፡


መልካም ዕለተ ሰንበት!