አንተ ማነህ? ማነኝ ብለህ ታስባለህ? 

እንደ አብዛኞቻችን ከሆንክ ስለራስህ ማንነት፣ ተፈጥሮና አሰራር ያለህ አመለካከትና እምነት በጣም የተዛባ የመሆን ዕድልህ ከፍተኛ ነው። ለማንኛውም ከላይ የተነሱትን ጥያቁዎች በመረዳት ስለራስህ ያለህን አመለካከት እና እምነት ምን እንደሚመስል ፈትሽ፡፡

 እነዚህን ጥያቄዎች በአግባቡ ለመረዳት እና ተቀራራቢ መልስ ለመስጠት ስለሰው አፍጣጠፍና ምንነት ማወቅ፣ ከተወለድክ እስከ 12 ዓመትህ ከማን ጋር እንደነበርክ ማስታወስ እና ከ12 ዓመት ጀምሮ እስከ አሁኗ ቅፅበት ድረስ ጊዜህን ከማን ጋር እና በምን እንደምታሳልፍ እንዲሁም ትኩረትህን በምን ላይ እንደምታደርግ ቆም ብለህ ማስተዋል ይጠበቅብሃል፡፡

ስለ ራስህ እና ስለ ነገሮች ያለህ አመለካከት የግዴታ ከሁለት አዱ ማለትም አዳጊ (growth mindset) ወይ  ውስን (fixed mindset) ነው የሚሆነው፡፡ 

ስለራስህ ያለህ አመለካከት አዳጊ (growth mindset) ከሆነ አሁንኑ ስኬታማ እንደሆንክ፣ ከዚህ የበለጠ ስኬታማ እንደምትሆን፣ ስኬታማ ለመሆን ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በሙሉ በውስጥህ እና በዙሪያህ እንዳሉ እና አሁንኑ መኖራቸውን እንኳን ባትረዳ ሲያስፈልጉህ እንደምታገኛቸው፣ አምላክህና ተፈትሮ በጥረትህ ልክ ሁሉንም ነገር ያለገደብ እንደሚሰጡህወዘተረፈ ታስባለህ እንዲሁም ታምናለህ፡፡ 

ስለራስህ ያለህ እምነት ውስን (fixed mindset) ከሆነ ደግሞ አሁን ስኬታማ አይደለሁም፣ ለስኬት የሚሆን አንዳች ነገር እና ማንነትም የለኝም፣ በመሆኑም ስኬታማ መሆን አይችልም፣ አምላኬ እና ተፈጥሮ ፊታቸውን አዙረውብኛል፣ ዕድለኛ አይደለሁም፣ ኑሮየም ከባድ ነው ... ወዘተረፈ ብለህ ታስባለህ እንዲሁም ታምናለህ፡፡

በጣም የሚገርመው ምስጢር ግን ከሁለቱ የትኛውንም ብቻ አንዱን ብታስብ እና ብታምን ትክክል ነህ፡፡ ምክንያቱም የምታስበው እና የምታምነው ማንውም ነገር ይሆንልሃል ይደረግልሃልና፡፡ 

ስኬታማ ነኝ፣ የበለጠ ስኬታማ እሆንማለሁ ብልህ ካሰብክ እና ካመንክ ትክክል ነህ፡፡ ስኬታማ ነህ የበለጠ ስኬታማ ትሆንማለህ፡፡ 

ስኬታማ አይደለሁም፣ ስኬታማ መሆንም አልችልም ብልህ ካሰብክ እና ካመንክም ትክክል ነህ፡፡ ስኬታማ አይደለህም፣ የበለጠ ስኬታማ መሆንም አትችልም፡፡ 

ለዚህ ነው ሰው በአእምሮው ያሰበውን እና በልቡ ያመነውን ማንኛውም ማንነት መሆን ይችላል የተባለው፡፡ 

ዋናው ጥያቄ ግን የቱን ማሰብ፣ ማመን እና መሆን ይሻልሃል ነው፡፡ አሁንኑ የሚሆንህን በአእምሮህ አስብ፣ በልብህ እመን እና መሆን ያለብህን በሃሳብ እና በእምነትህ መሰረት ትሆናለህ፡፡

ለሁለት የተከፈለ ቲማቲም አስገራሚ የውስጥ ዕይታ (በአለባቸው ታዴ ሀምሌ፣ 2014 ዓ.ም)



አሁን ራስህን ገምግመህ ልታገኝ የምትችለውን ውጤት እንመልከት:-

አንደኛ ስለራስህ ያለህን አመለካከት እና እምነት ገምግመህ ስለራስህ አዳጊ አመለካከት (growth mindset) እና እምነት አለህ እንበል፡፡ 

ይህ ከሆነ አሁንኑ ስኬታማ እንደሆንክ፣ ከዚህ የበለጠስኬታማ እንደምትሆን፣ ስኬታማ ለመሆን ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በሙሉ እንዳሉህ እና አሁንኑ ከሌሉም ሲያስፈልጉህ እንደምታገኛቸው፣ አምላክህና ተፈትሮ በጥረትህ ልክ ሁሉንም ነገር እንደሚሰጡህወዘተረፈ ታስባለህ እንዲሁም ታምናለህ፡፡ 

በዚህም እንኳን ደስ አለህ፡፡ ነገር ግን ልብ በል ስኬት ሂደት እንጅ መጨረሻ የለውም እና አሁን ካለህበት በጣም በለጠ ስኬታማ መሆን ትችላለህ እና አሁን ካለህበት የበለጠ ስኬታማ የምትሆንበትን መንገድ አስብበት፡፡ 

ሁለተኛው ስለረስህ ውስን አመለካከት (fixed mindset) እና እምነት አለህ እንበል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ስኬታማ አይደለሁም፣ ለስኬት የሚሆን አንዳች ነገር እና ማንነት የለኝም፣ በመሆኑም ስኬታማ መሆን አይችልም፣ ፈጣሪ እና ተፈጥሮ ፊታቸውን አዙረውብኛል፣ ኑሮየ ከባድ ነው ... ወዘተረፈ ብለህ ታስባለህ እንዲሁም ታምናለህ፡፡ 

አሁንም በድጋሜ እንኳን ደስ አለህ፡፡ የህይወት ስኬት መጀመሪው አሁን የት እንዳሉ ማወቅ ነውና፡፡ ለምን እንደሆነ ታውቃለህ፤ ብዙ ሰዎች ስለራሳቸው ቁጭ ብለው አስበው እና ራሳቸውን ገምግመው አያውቁም፡፡ 

ይልቁንም ብዙ ጊዚያቸውን እና ትኩረታቸቨውን የሚያባክኑት ከቴሌቪዥናቸው ጋር፣ ሌሎች ግለሰቦች ያዘጋጁላቸውን መርሃ ግብሮች በመከታተል፣ ከሰዎች ጋር መንግስትን ወይም ሰዎችን በመተቸት እና ለፖሊሲ ግብዓት የማይውል አስተያየት በመስጠት፣ ጭንቀታቸውን መከላከል ወደ አልባሌ ቦታ በመሄድ ጊዜ እና ትኩረታቸውን ያባክናሉ:: ስለሆነ ራሳቸውን ለመገምገም ጊዜ እና ትኩረት የላቸውም፡፡ 

እኒህ ዓይነት ሰዎች በዘፈቀደ ያገኙትን ህይወት ይኖራሉ፡፡ ህይወት ወደ እነርሱ በዘፈቀደ እና በድንገት ትመጣባቸዋለች እንጅ እነሱ ህይወታቸውን አየሰሩም፣ አይኖሩምም፡፡

አንተ ግን እንደነሱ ማድረግ እና በዘፈቀደ መኖር ስትችል ይሄው ከብዙዎ በተለየ መንገድ ከምንም በፊት የራሴ ህይወት ያሳስበኛል በማለት ቁጭ ብለህ ራስህን በመገምገም የስኬትን ጉዞ መጓዝ ጀምረሃል፡፡ 

በዚህም በጣም ደስ ይበልህ የስኬት መጀመሪው አሁን የት እንዳሉ መገምገም እና ማወቅ ነውና፡፡ 

ይህን የራ ግምገማ በማድረግህ ብቻ በጣም ብዙ ጊዜና ትኩረትህን ለራስህ ታደርጋለህ። ወደ ራስህ የመመልከት ዕድልም ይፈጥርልሃል። 

በዚህም ጊዜ ህይወት እንዲሁም ስኬትመዳፍህ ስር መሆኗበግልፅ ትገነዘባለህ። በእርግጥ አሁን የገመገምከው ስላመለካከትህ በተለይም ለራስህ ስላለህ ስላመለካከት ብቻ ነው፡፡ 

ሁሉም ሰው በተመሳሳይ እኩል አቅም እና ችሎታ አለው የተሰጠው መክሊት ቢለያይም የሚለው እውነታም ጥርት ብሎ ይገባሃል። ሆኖም በጣም ጠንካራ ስራ እንደሚጠብቅህ ማወቅ አለብህ፡፡ 


የቤት ስራ:-

ካመለካከትህ በተጨማሪ ከስኬታማነትህ ከልማዶችህ፣ ከስዕብናህ፣ ከስሜትህ፣ ከውታማነትህ ... ወዘተ አንጻር ራስህን ገምግም


ውድ አንባ ለእርስዎ ስኬታማ ህይወት ማለት ምን ማለት ነው?

መልሱን በዚህ ምለሱን ፃፉልን!

እንዲሁም ጥያቄ፣ አስተያየት፣ ተጨማሪ ሃሳብ ካለ በዚህ ድህረ-ገጽ ፃፉልን! 

መልካም ንባብ