መግቢያ

አእምሯችን በአግባቡ ከተጠቀምንበት ታማኝ አገልጋይ መሳሪያችን ነው፡፡ ባግባቡ ካልተጠቀምንበት ደግሞ ቀንደኛ ጠላታችን ነው፡፡ ብዙ ሰው አእምሮው እሱን ይጠቀምበታል እንጅ እሱ አእምሮውን አይጠቀምበትም፡፡በመሆኑም አእምሮህ ስለ ራስህ፣ ስለ ሌሎች እና በአጠቃላይ ስለ ነገሮች እና ስለ ክስተቶች ያለህን አመለካከት ይወስናል፡፡

የአእምሮ ክፍሎች

ሁለት የአእምሮ ክፍሎች አሉን፡፡ ንቁ አእምሮ እና ድብቁ አእምሮ ናቸው፡፡ 

ንቁ አእምሮ

ንቁ አእምሮ አመዛዛኝ እና የፈለገውን ሃሳብ ወይም ነገር ሲፈልግ ይቀበላል፤ ሳይፈልግ ዳግሞ ውድቅ ማድረግ ይችላል፡፡ 

ንቁ አእምሮ አምኖበት የተቀበለውን ሃሳብ ወይም ነገር ወደ ድብቁ አእምሮ በመላክ፣ ድብቁ አእምሮ ደግሞ ሰውነታችን አስፈላጊውን ስሜት እንዲሰማ በማድረግ ድርጊት እንዲፈጽም ያደርጋል፡፡ 

በዚህም አሰራር መሰረት ንቁ አእምሮ ድብቁን አእምሮ ይቆጣጠራል ማለት ነው፡፡ 

ንቁ አእምሮ መረጃን የሚያገኘው በአምስቱ የስሜት ህዋሳቶቻችን ማለትም በማየት፣ በመቅመስ፣ በማሽተት፣ በመስማት እና በመዳሰስ ነው፡፡ 

ንቁ አእምሮ በአውሮፕላን አብበራሪ ይመሰላል፡፡ አውሮፕላን አብራሪ የፈለገውን የአውሮፕላን ፕሮግራም በመንካት የአውሮፕላኑ ፕሮግራም ደግሞ አስፈላጊውን የአውሮፕላን ክፍል ተገቢውን ምላሽ ወይም ድርጊት እንዲፈጽም ያደርገዋል፡፡ 

በተመሳሳይ ንቁ አእምሯችን ድብቁ አእምሯችን ን መረጃ በመስጠት አስፈላጊ እርምጃ እንድንወስድ ወይም እንዳንወስድ ያደርገናል፡፡

አስቡት በዚህ የመረጃ ልውውጥ ጊዜ ንቁ አእምሮ ትክክል ያልሆነ መረጃ ወደ ድብቁ እምሮ እንዲገባ በፈቅድ የድብቁ አእምሮ ብቸኛው አማራጭ መረጃውን መቀበል እና መረጃውን የሚመጥን ስሜት እንዲሰማን በማድረግ ሰውነታችን እርምጃ እንዲወስድ እና ተመጣጣኙን ውጤት ይሆናል፡፡

ድብቁ አእምሮ

ድብቁ አእምሮ የማያመዛዝን እና ንቁ አእምሮ ተቀብሎ የሰጠውን ማንኛውንም ሃሳብ ወይም ነገር ያለምንም ማንገራገር ይቀበላል፡፡ 

በንቁ አእምሮ ተቀባይነት አግኝቶ በድብቁ አእምሮ የተቀመጠ ማንኛውም ሃሳብ (ልማድ ወይም ሱስ) አካልን ሳይፈልግ በግድ አስፈላጊውን ድርጊት እንዲወስድ ያደርጋሃል፡፡ 

ድብቁ አእምሮ መረጃ የሚቀበለው በስሜት መልከ ያለን ሃሳብ ነው፡፡ 

ድብቁ አእምሮ በለም አፈር ይመሰላል፡፡ ለም አፈር ሆን ተብሎ የተዘራበትን ወይም ባጋጣሚ ያገኘውን ማንኛውም መልካም ዘር ወይም እንክርዳድ ወይም አረም እኩል ያበቅላል፡፡ 

ድብቁ አእምሮም የሚሰራው እንዲሁ ነው፡፡ ሆነ ተብሎ የተሰጠውን ወይም ባጋጣሚ ያገኘውን ማንኛውም አዎንታዊ ወይም አሉታዊ፣ መልካም ወይም መጥፎ፣ ጠቃሚ ወይም ጎጅ ሃሳቦችን እኩል በመቀበል እና ልማድ ወይም ሱስ በማድረግ፣ አስፈላጊውን ስሜት እንዲሰማን በማድረግ ሰውነታችን ድርጊት እንዲወስድ ያደርጋል፡፡ 

ለዚህም ነው አንድ ሰው አንድን ጥሩ ይሁን መጥፎ ሀሳብ ደጋግሞ ሲያስበው እና ሲያምነው ብሎም ሲተገብረው ከተወሰነ ድግግሞሽ በኋላ ድርጊቱ መጥፎነቱን ተረድቶት ሊያቋርጠው ቢፈልግ እንኳ ለማቋረጥ በጣም የሚቸገረው፡፡

የድብቁ አእምሮ አሰራር 

የሰው ልጅ ነኝ ብሎ ያሰበውን እና ያመነውን ነገር በሙሉ ይሆናል፡፡  

አንድ ሰው በአእምሮው ውጤታማ ነኝ፣ የበለጠ ውጤታማ እሆናለሁ ብሎ ካሰበ እና ይህንንምሃሳብ በልቡ ካመነው እውነት ነው ሰውየው ያለጥርጥር ስኬታማ ነው፣ ከዚህ የበለጠም ስኬታማ ይሆናል፡፡ 

እንዲሁም ይህ ተመሳሳይ ሰው በአእምሮው ውጤታማ አይደለሁም፣ ወደፊትም ውጤታማ መሆን አልችልም ብሎ ካሰበ እና ይህንንም ሃሳብ በልቡ ካመነው እውነት ነው ሰውየው ያለጥርጥር ኪሳራ ነው፣ ወደፊትም ስኬታማ መሆን አይችልም፡፡ 

ድብቁ አእምሮን መጠቀም

ሰውየው ነኝ ብሎ አስቦ ወይም ሳያስበው ያመነውን ማንኛውም ሃሳብ ድብቁ አእምሮ በእምነት እና በእውነታነት መልኩ ያስቀምጠዋል፡፡ 

ከዚም እምነት እና እውነታ ጋር የተገናኙ ማንኛውንም ነገሮች እና ሁኔታዎች በሂደት በሰውየው ህይወት በአካል እንዲገለጥ ያደርጋል፡፡ 

ስለዚህ በውስጣችሁ ነኝ ብላችሁ የምታስቡትን ነገር መርምሩ፣ እወቁም፡፡ የምትወዱት ከሆነ መልካም ነው ይሆን ይቀጥል፤ ካልወደዳችሁት ግን ሃሳባችሁን በመቀየር እምነት እና እውነታችሁን አሀኑኑ መቀየር ትችላላችሁ፡፡ ሃሳብ ርግብግቢቱን በፈለገነው መልኩ የምንቀይረው ሃይል ነውና፡፡ 

ይህም የሚሆነው ንቁ አእምሯችን በሰመመን ውስጥ በሚሆንበት ከምኝታ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት እና ከእንቅልፋችን እንደነቃን በተመስጦ ውስጥ በመሆን እና ምናባዊ እይታን በመጠቀም የምንወደውን ሃሳብ ወደ ድብቁ አእምሯችን ያለምንም ከልካይ ቀጥታ በማስገባት እና ይህንን የምንወደውን ሃሳብ የሚመጥን እምነት እና እውነታ መፍጠር አንችላለን፡፡ 

ይህም ሰው ልጆች ታላላቅ ስጦታዎቻችን ዋናዎቹ ናቸው፡፡ እንስሳት እና እጽዋት እንዲሁም ደቂቅ ዘአካላት ይህንን ማድረግ አይችሉምና፡፡

እንግዲህ ውድ አንባቢየ ከጽሁፉ እንደተረዳኸው ህይወታችንን መጠቀም እና መቆጣጠር ማለት እኒህን ሁለት አእምሮዎቻችን ምን እንደሆኑ እና እንዴት አንደሚሰሩ በመረዳት ወደ እነሱ የሚደርሰውን መረጃ በሙሉ መቆጣጠር ማለት ነው፡፡ 

ምክንያቱም የእያንድንዱ የየቅጽበት እና የዕለት ተዕለት ሃሳባችን፣ ድርጊታችን እና ውጤታችን የሚወሰነው እና በህይወታችን ስኬታማ ወይም ኪሳራ የምንሆነው በዚሁ ሂደት ነው፡፡ 

ለትም በንቁ አእምሯችን በአምስቱ የስሜት ህዋሳት በተቀበልናቸው የውጭ መረጃዎች እና እነዚህን መረጃዎች ወደ ድብቁ አእምሯችን ውስጥ ገብተው እንዲቀመጡ በመድረግ እና ድብቁ አእምሯችን በምላሹ ሰውነታችን አስፈላጊውን ስሜት እንደሰማው አና ድርጊት እንዲፈጽም በማድረግ ነው፡፡ 

ሰው የዘራውን ያጭዳል

መልካም ዘር የዘራ ማለትም በንቁ አእምሮው በአምስቱ የስሜት ህዋሳት መልካም ሃሳብን ወይም ነገርን ከውጭ ወደ ውስጥ ወደ ድብቁ አእምሮው ያስገባ፣ መልካም ፍሬን ያጭዳል ማለትም በህይወቱ መልካም ስሜት፣ ድርጊት እና ውጤትን ያገኛል፡፡

ድብቁ አእምሮ የስሜት መገኛ ነው

የፍርሃት፣ የሃፍረት፣ የንዴት፣ የጭንቀትወዘተ ስሜቶች በሙሉ በህይወታችን የሚፈጠሩት ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ነው፡፡ መገኛቸው ወይም መቀመጫቸው ድብቁ አእምሮ ነው፡፡ 

ሳናስበውና ሳናቅደው ምናልባትም ከቁጥራችን  በሚመስል መንገድ የፍርሃት፣ የሃፍረት፣ የንዴት፣ የጭንቀትወዘተ ስሜቶች በዕለት ተዕለት ህይወታችን በተደጋጋሚ በመከሰት ስሜታችንን፣ ድርጊታችንን እና ጤቶቻችንን በተመሳሳይ ዑደት ውስጥ እንዲመራ ደርጋሉ፡፡ 

ደስ ሚለው ዜና ግን አንድ የሁለቱን አእምሮዎች ምንነት እና አሰራር በሚገባ የተረዳ ሰው ያለበት የኑሮ አካባቢ እና ሁኔታ መቀየር ስፈልገው በነዚህ ስሜቶች አማካኝነት የሚደርስበትን የህይወት ኪሳራ ዑደት መስበር እና የሚፈልገውን መልካም ስሜት እና ስኬታማ ህይወት ማለትም በፍቅር፣ በደስታ፣ በሃብት፣ በብልጽግናወዘተ የተሞላ ህይወት መኖር ይችላል፡፡ 

ይህ እንዴት ይሆናል?

ጥያቄ፣ አስተያየት፣ ተጨማሪ ሃሳብ ካለ በዚህ ድህረ-ገጽ ፃፉልን!

መልካም የንባብ ጊዜ እመኛለሁ!