መነሻ ሃሳብ

እኛ ሰዎች ፈተናዎች ሁሉ በላይ ነን፡፡ ምክንያቱም እኛ ሰዎች ማደግ እና መሻሻል የተፈጥሮ ልምምድና ጠባያችን ነው፡፡ ማለትም በየወቅቱ ከሚገጥሙን ፈተናዎች በላይ የተሻለ አስተሳሰብ፣ ስዕብና፣ ልምድ ... ማዳበር፣ ሰም እንምችላለን:: በአንፃሩ ፈተናዎች ግን አያድጉም ይልቁንም ሁል ጊዜ ባሉበት ይቆያሉ፡፡ የማደግ ልምምድ፣ ጠባይና ችሎታ የላቸውም፡፡

እኛ ሰዎች እናድጋለን፣ ፈተናዎች ግን ኣያድጉም

ለዚህ ማሳያ የምትሆነን አንድ ከዶ/ር እዮብ ማሞ 25 የስኬት ቁልፎች ከሚለው መጽሐፉ ሳነብ ያኘኋትን በህይወቴ ትልቅ ትምህርት የሆነችኝን ታሪክ ላካፍላችሁ ወደድሁ፡፡ እናንተም እንደምትማሩባት እና ከዚህ በኋላ በህይወታችሁ የሚገጥማችሁን ማንኛውም ፈተና የምታዩበት መንግድ እንደሚለወጥ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ አንድ ወቅት አንድ ሰው በቻይና አገር በሚገኘው በከፍታው የዓለም ትልቁ ወደ ሆነው ኤቨረስት ተራራ ለመውጣት ሞክሮ ባቃተው ጊዜ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ ኤቨረስት ሆይ አንተ አታድግም እንዲሁ ነህ፡፡ እኔ ግን ሰው ነኝ እና በልምድ አድጋለሁ እና በልምድ ራሴን አሻሽ አንድ ቀን አሸንፍሃለሁ ሲል በተራራው ላይ ዛተበት፡፡

እንዳለውም ኤቨረስት ተራራ ባለበት ተኝቶ እንቅልፉን እያጣጣመ ባለበት ወራት እና ዓመታት ሰውየው ከብዙ ልምምድ በኋላ ራሱን በማሻሻል ወደ ተራራው አናት ወጣ፡፡ እንደተናገረውም ኤቨረስትን አሸነፈው፡፡ እሱም ብቻ አይደለም፣ ከኤቨረስት ተራራ አናት ላይ በመውጣት በዓለም ካሉት በብሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሁሉ ከፍ ብሎ ታየ ይላል፡፡


ሰው ከፈለገ ይህንን ለሳምንታት የሚቆይ የበረዶ ክምር ተቋቁሞ ሃገሩን ያሳድጋል:: 

በሞሊሲ ከተማ ከሳምንት በላይ የቆየው የበረዶ ክምር የካቲት፣ 2014 ዓ.ም በጸሓፊው የተወሰደ


ሰው ካልፈለገ ኢትዮጵን የመሰለች ሃገር ባለችበት ለዘመናት ተኝቶባት ይኖራል:: በእርግጥ ይህ የእያንዳንዳችን እጅ ያለበት እንደ ሃገር በጋራ እየሰራነው ያለ ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡ ሆኖም ግን የጽሁፉ ዋና ትኩረት ግለሰቦች ላይ ነው:: ምክንያቱም ግለሰቦች ራሳቸውን መቀየር ከቻሉ ሃገር የግለሰቦች ስብስብ ናትና፡፡ እንዲሁም እንደ ለሰብ ራስን ማሻሻል በራስ ሙሉ ፈቃድ የተመሰረተ ስለሆነ በተነፃፃሪ ቀላል ነው፡፡ ቡድኖችን ማሻሻል ግን የተለያዩ ሰዎችን ፈቃድ የሚጠይቅ በመሆኑ ብዙ ጥረት የሚፈልግ ከራሳችን በመቀጠል የምናስብበት የቤት ስራ ነው፡፡

ስለሆነም እያንዳንዳችን እንደ ግለሰብ በትናንሽ ፈተናዎች ምክንያት ስላልፈለግን ተኝተንባቸው ያለናቸው ከፈለግን ግን ታሪክ ልንሰራባቸው የምንችላቸው መልካም አጋጣሚ ምድን ቸው? 

እንግዲህ ወደ ርዕሰ ጉዳያችን ስንመለስ ፈተናዎቻችን መልካቸው ቢለያይም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ሁል ጊዜም ባለህበት እርገ ናቸው:: ባሉበት ሆነው ነው የሚኖሩት አያድጉም፡፡ እኛ ሰዎች ግን አእምሯችን ተጠቅመን በማደግና በመሻሻል ከፈተናዎች በላይ የመሆን የተፈጥሮ ጸጋ እግዚአብሔር አምላክ በነፃ ሰጥቶናልና እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ነገር ግ ስንቶቻችን ይህንን ስጦታ በአግባቡ እንደምንጠቀመው እግዚአብሔር ይወቀው፡፡

አስቡት ያ ሰው በመጀመሪያው ሞክሮ ሲያቅተው ተስፋ ቆርጦ እንደገና ሳይሞክር ቢቀር ምን እንደሚያጣ እና ምን እንደምጣ ልብ በሉ፡፡ ይህን ከዓለም ህዝብ ከፍ ብሎ የመታየት ታሪካዊ ስኬት አይቀዳጅም ነበር፡፡ እንዲሁም እኛን በፈተና ጊዜ እንንበረታ እና ደጋግመን መሞከር እንዳለብን አያስተምረንም ነበር፡፡

አሊያም ያ ሰው አንድ ጊዜ እንደሞከረ ወደ ተራራው ቢወጣ ኖሮ ያን ያህል ልምድ፣ ትዕግሰትና ብስለት አይኖረውም ነበር:: ሰውየው ወደ ኤቨረስት ተራራ ለመውጣት በመጀመሪያው ዙር መሸነፉን የበለጠ ልምድ እና ትዕግስት እንዲሁም ብስለት እንዲኖረው እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቀመበት፡: 

በጣም የሚያሳዝነው ነገር ግን ብዙዎቻችን አንድ ፈተና ሲገጥመን ከእኛ የማደግ እና መሻሻል የተፈጥሮ ጸጋ ካለው ድንቅ ማንነታችን ይልቅ ፈተናው ገዝ ይታየን እና ገና ፈተናውን በማሰብ አንድ ጊዜም ሳንሞክር በሃሳብ ነው ተስፋ የምንቆርጠው፡፡  

ለምን? የልምምድን ምስጢር እና  ከፈተናዎች ሁሉ በላይ መሆናችንን ስለማንገነዘብ፡፡

ለማንኛውም ለግንዛቤ ያህል ጥቂት ጥያቄዎች እናንሳ፡-

ለእናንተ የምትፈልጉትን ሰው ለመሆን፣ የምትፈልጉትን ለማግኘት እና የምትፈልጉትን  ለመስራት  እንደ ኤቨረስት ተራራ የሆነባችሁ ፈተና ምድን ነው?

ይህን እና ወደፊትም በየህይወት ቅጽበታችሁ የሚገጥሟችሁን ፈተናዎች ለማሸነፍ ለራሳችሁ ምን ቃል ትገባላችሁ?

ከዚህ ታሪክ የተረዳችሁትን ጭብጥ ሃሳብ ባጭሩ በራሳችሁ ፃፉ

 

አንዴ ቆም ብለህ አስብ፡--

ዛሬ አሁንኑ ልትተገብረው የምትችለው ከዚህ ጽሁፍ የተማርከው አንድ ... ሁለት ... ሶስት ... ወዘተ ሃሳብ ምንድን ነው?  

o ስላንድ ነገር ብዙ መረጃ መኖር ዕውቀት ነው፤ መረጃውን በተግባር መጠቀም ደግሞ ጥበብ ነው እና አሁንኑ ዕውቀቱን በተግባር በመጠቀም አንድ እርምጃ ወደ ፊት

 

አስተያየት ተጨማሪ ሃሳብ እንዲሁም ጥያቄ ካልህ በዚሁ ድህረ-ገጽ ፃፉልን!

 

ሰው ከፈተናዎች ሁሉ በላይ ነው፡፡ ሰው በልምምድ ያድጋል፣ ይሻሻላል፣ ፈተናዎች ግ አያድጉም!