የመነሻ ሃሳብ
ሁላችንም እንደምናውቀው ልጆቻችን በቀን ለብዙ ሰዓታት ምናልባትም ከ8 በላይ ሀለመ… ABC… እና 123 …ን በጣም ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተማሩ ነው፡፡ በእርግጥም ይህ በጣም ደስ ይላል፡፡ ነገር ግን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በእውኑ ለልጆች የወደፊት ሁለንተናዊ ህይወት ስኬት ሀለመ… ABC… እና 123 …ን ብቻ መማር በቂ ነውን? አሁን እየሆነ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እኔ አይመስለኝም፡፡
እንደ
እኔ እይታ እንዲያውም በአብዛኛው በቀለም ትምህርት ጎበዝ የሆኑ የትኛውም ደረጃ ያሉ ልጆች ከኬጂ እስከ ዩኒቨርሲቲ በብዙ ወሳኝ
የህይወት ክፍላቸው ለምሳሌ አብሮ በመኖር ወይም ግንኙነታቸው፣ በህይወት የሚገጥማቸውን ተግዳሮት ወይም ገጠመኝ በብልሃት የማለፍ
አቅማቸው፣ የራሳቸውን አና የሰዎችን ስሜት የመገንዘብ፣ የመጠበቅና የማስተዳደር ችሎታ … ወዘተ ተግዳሮቶች ውስጥ በቀላሉ
የመውደቅ እና በህይወታቸው የማይጠበቅ የስዕብና ቀውስ ውስጥ ሲገጥማቸው ይታያል፡፡
በመሰረቱ በህይወት ስኬታማ ለመሆን ያን ያህል ከፍተኛ የቀለም ትምህርት ደረጃ ግድ አይደለም፡፡ ለዚህም ማሳያው ብዙ የዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችን ታሪክ ስንመለከት ብዙዎቹ የቀለም ትምህርት የተማሩ አይደሉም ወይም ትምህርት ያቋረጡ ናቸው፡፡ ይልቁንም መፍጠር በሚፈልጉት እሴት እና ወሳኝ በሆኑ የህወት ዘርፎቻቸው ጠልቀው በማጥናት እና በመመራመር እና የህወትን ትምህርት ከራሳቸው ተግባራዊ የህይወት ገጠመኞቻቸውን በመቀመር የተማሩትን እና የተገነዘቡትን ዕውቀት ወዲያውኑ በራሳቸው ላይ የተግባር ሙከራ ያደርጋሉ፡፡
ይህ ስለምን ሆነ?
እንደምናውቀው ተማሪዎች በትምህርት ቆታቸው ብቸኛው ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት የሚማሩት ነገር ቢኖር በቀለም
ትምህርት ጥሩ ውጤት በማምጣት በተሻለ የመንግረሰት እና የግል ተቋም የተሻለ ተቀጣሪ እንዲሆኑ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ በተሻለ
የመንግሰት እና የግል ተቋም የተሻለ ተቀጣሪ መሆን የአብዛኛው ተማሪ የህወቱ ዓላማ እና ግብ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ነገር ግን ህይወት በቀለም ትምህርት ከመጎበዝ የበለጠች ናት:: በመሆኑም ተማሪዎች የትምህርት ቆይታቸውን ጨርሰው ወደ መደበኛ ህይወታቸው ጉዞ ሲጀምሩ ህይወት ቀለም ትምህርት የበለጠ ጥያቄዋን እና ፈተናዋን ታቀርብልናለች፡፡ ያኔ በትምህርት ቆይታችን እኛ በትኩረት የተማርነው ስለ ቀለም ትምህር ነው፤ የህይወት ዓላማና ግባችንም በተሻሉ ተቋት ለመቀጠር ነበር፡፡ በመሆኑም ላም ባልዋለበት ኩበት እነደማይለቀም ሁሉ ተማሪዎችም ያልተማሩትን ፈተና መመለስ ይሳናቸዋል፡፡ እናም በህይወት ፈተና ተፈትኖ ወድቆ ከመነሳት ይልቅ ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡ የማይፈልጉትን ህይወት መምራት ተላምደው ይኖራሉም፡፡
ይህን
እንዴት አወኩ?
እኔ በራሴ ህይወት ከ20 ዓመታት በላይ የትምህርት ቆይታዬ በኋላ ያለኝ የህይወት ደረጃ (ማለትም የ12 ዓመት ት/ቤት፣ 3 ዓመት የመጀመሪ ዲግሪ፣ 2 ½ ዓመት የ2ኛ ዲግሪ እና አሁን እየተማርኩ ያለሁትን 2 ½ ዓመት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርት ጨምሮ) እና ተግዳሮቶችን እየፈታሁ ያለሁበት መንገድ ህያው ምስክር ነው፡፡ እንዲሁም ከ10 ዓመታት በላይ ባለኝ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የማስተማር ቆይታየ በተማሪዎቸ ህይወት በተግባር አይቸዋለሁ፣ እያየሁትም ነው፡፡
ስለሆነም እንዲህ ቢሆንስ (መፍትሄ)?
እንደ
ቀለም ትምህርት ማለትም ሀለመ… ABC… እና 123 … ሁሉ ከተቻለም በበለጠ ተማሪዎች በትምህር ቤት ቆይታቸው ስለ ህይወት ስኬት እና የህይወት ስኬትን
ሊጎናጸፉ ስለሚችሉባቸው መንገዶች እና ስለሚያስፈልጉ ነገሮች በአጠቃላይም ስለሁለንተናዊ የህይወት ስኬት በጥልቅ
ቢማሩስ፡፡ እንዲሁም ለመንግስት ተቀጣሪነት ሳይሆን ለራሳቸውን እና ለሌሎች ስራ ስለመፍጠር ትኩረት
አድርገው ቢማሩስ?
ከላይ
እንደተገለታው ልጆቻችን በቀን ብዙ ሰዓታት ምናልባትም ከ8 በላይ ሀለመ… ABC… እና 123
…ን በጣም ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ይማራሉ፡፡ በዚህም ጥቂቶች በቀለም ትምህርታቸው ጎበዝ ይሆናሉ፡፡ ብዙዎቹ
ግን ውጤታማ አይሆኑም፡፡ ችግሩ በትምህርታቸው ውቴታማ መሆን አለመሆናቸው አይደለም፡፡
እናም ትምህርት
ቤቶች አንድም በትምህርት ቤታቸው የትምህርት ስርዓት ከቀለም ትምህርት ባሻገር ለተማሪዎች በህይወታቸው በተጨባጭ የሚጠቅሟቸውን
ሌሎች የህይወት ዘርፎች ቢያካትቱ፣ ተማሪዎችን በተሻለ ተቋትም ከመቀጠር በተጨማሪ በተማሩት ትምህርት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ
እንዴት በራሳቸው ስራ መፍጠር እና ሌሎችንም መርዳት እንደሚችሉ የሚማሩበት መንገድ ቢፈጠር፡፡
በእርግጥ ት/ቤቶች ተማሪዎችን ከላይ በመፍትሄ መልኩ በተጠቀሰው መንገድ እንኳን ቢያስተምሩ የተማሪዎች የህይወት ስኬት በት/ቤቶች ጥረት ብቻ እውን ለማድረግ እጅግ ፈታኝ ነው፡፡ ምክንያቱም ተማሪዎች ከት/ቤታቸው የቆይታ ጊዜ በተጨማሪ በቀጥታ ከቤተሰቦቹ ጋር እና በተዘዋወሪ ከአካባባው ማህበረሰብ በሚያደርጉት መስተጋብር ሌላው የተማሪዎች የህይወት ስኬት ወሳኝ ነገር ነውና፡፡ ምክንያቱም ተማሪዎች ምንም እንኳ ት/ቤት በሚገባ ቢማሩ ወደ ቤተሰባቸው እና አካባቢያቸው የሚሰሙት እና የሚያዩት ነገር በእጅጉ ወሳኝ ነው፡፡ ይህም በሁለችንም አካባቢ በአብዛኛው በተግባርም ይታያል፡፡
ስለሆነ በበኩሌ ሌላው መፍትሄ ብየ የማስበው በት/ቤቶች የወላጆች ቀን በዓመት አንዴ ከሚኖር ይልቅ የወላጆች ት/ቤት ቢኖርስ፡፡ ይህ እስካልሆነ ድረስ ግን ወደድንም ጠላንም፣ አመንም አላመንም ተማሪዎች በህይወታቸው የሚችሉትን ያህል በህወታቸው ሁለንተናዊ ስኬትን ሊጎናጸፉ አይችልምና እናስብበት፡፡
አስተያየት ተጨማሪ ሃሳብ እንዲሁም ጥያቄ ካልህ በዚሁ ድህረ-ገጽ ፃፉልን!
0 አስተያየቶች