በእውነት የትውልድ ቅብብሎሽ ትወናን ቆም ብሎ ላሰበው ሰው እጅግ በጣም ግራ ያጋባል፣ ያሳስባልም፡፡

በአንደኛ ደረጃ ገና ከጨቅላነታችን የራሳችን የምንለው ህይወት ከመመስረታችን በፊት ባለው ዕድሚያችን ሁሉም የህይወት ምርጫዎቻችን እና ውሳኔዎቻችን በወላጅ ወይም በአሳዳጊ ወይም በተንከባካቢ ይመረጣል፣ ይወሰኑልናልም፡፡ 

ጉዳዩ በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ እግረ-መንገዳችንን በሚቀጥለው የራሳችን ህይወት ስንጀምር የህይወት ምርጫ እና ውሳኔ እንዴት እንደሚመረጥ እና እንደሚወሰን እንማራለን፡፡ 

ይህንንም ሂደት የህይወት ግንባታ ቁጥር አንድ ብየዋለሁ

በሁለተኛ ደረጃ ዕድሚያችን ለትምህርት ሲደርስ በማንነታችን ግንባታ ላይ ዩድርሻቸውን ለመወጣት ትምህርት ቤቶቻችን በመምህራን እና በሰራተኞች አማካኝነት በተማሪ መልኩ ይረከቡናል፡፡ 

ከዛም መምህራን እና ሰራተኞች ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ ባገኙት አጋጣሚ እና በቻሉት መጠን የእነሱን ማንነት ወደ እኛ ያስተጋቡልናል፡፡

ምናልባት በሆነ አጋጣሚ ከተወለድንበት አካባቢ ርቀን ሄደን ካልተማርን በስተቀር የት/ቤቱ መምህራን እና ሰራተኞች የቀለም ትምህርት ከማወቅ ውጭ በማንነታቸው ከወላጆቻቸን፣ ከአሳዳጊዎቻችን ወይም ከተንከባካቢዎቻችን አይለዩም እና ያንኑ ማንነት ልክ በዐለት ላይ የተፃፈ ያሀል ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ያትሙልናል፡፡ 

ይህንንም ሂደት የማንነታችን ማረጋገጫ ሰነድ ብየዋለሁ 

ይህ በውስጡ እጅግ በጣም ውስብስ ሂደት ያለው የህይወት እና የትውልድ ቅብብሎሽ እንዲሁ በአጭር በጽሁፍ ሲገለጽ ነው፡፡ 

በእርግጥም እኔ በበኩሌ ከትውልድ ቅብብሎሽ ሂደት ጋር ምንም ተቃውሞ እና ቅሬታ የለኝም፡፡ ቢኖረኝም ምንም አላመጣም የተፈጥሮ ህግ እስከሆነ ድረስ እንዲሁ ትውልድ ሲያልፍ፣ ትውልድ ሲተካ ይቀጥላል፡፡ 

የወላጆችን፣ የአሳዳጊዎችን፣ የተንከባካቢዎችን በተጨማሪም የት/ቤት መምህራንን እና ሰራተኞችን በትውልድ ቀረጻ ላይ ያላቸውን አስተዋጽኦም አደንቃለሁ፡፡ 

እነሱ ያላቸውን እና ያወቁትን ይሰጣሉ፣ ያሳውቃሉም፡፡ ደግሞስ ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባል አይደል የሚባለው፡፡

አዚህ ሂደት ላይ አንድ ልብ ልንለው የሚገባው ሳይንሳዊ ሃቅ ግን ከልጅነት እና ከትምህርት ህይወታችን በኋላ አድገን እና የራሳችን የምንለው ህይወት ከመሰረትን ጀምሮ ለህይወታችን የሚሆኑ ሁሉንም ምርጫዎችን እና ውሳኔወችን የምንመርጠው እና የምንወስነው ባጠቃላይም የሚኖረን የህይወት ዓይነት ያኔ በልጅነት የህይወት ጉዟችን እግረ-መንገዳችን ከወላጅ፣ ከአሳዳጊ ወይም በተንከባካቢዎቻችን እንዲሁም ከትምህርት ቤት መምህራን እና ሰራተኞች ባየነው፣ በሰማነው፣ በተረዳነው መሰረት ይሆናል፡፡

እናም የእኔ ጉዳየ እነዚያ ከእግዚያብሔር በታች ትውልድን በአምሳላቸው የሚቀርጹ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ ተንከባካቢዎች እንዲሁም የት/ቤት መምህራን እና ሰራተኞች ራሳቸው የተቀረጹበት መንገድ ትክክል ባይሆንስ

በመሆኑም የህይወት ዘይቤያቸው ትክክል ባይሆንስ? የሚቀረጹት ትውልዶችስ እጣ-ፈንታቸው የቀራጺያቸውን የህይወት ዘይቤ መድገም አይደለምን?

በሶስተኛ ደረጃ ዛሬም እንኳ አድገን እና የራሳችን የምንለው ህይወት መስርተን ሳይቀር በእያንዳንዷ የጋራ ህይወታችን ብቻ ሳይሆን የግል ህይወታችንም ጭምር በተመለከተ የህይወት ምርጫዎቻችንና ውሳኔዎቻችን የሚመረጡልን እና የሚወሰኑልን በሌሎች ሰዎች ማለትም በጓደኞቻችን፣ በመንግስት እና ፖለቲካ፣ በመገናኛ ብዙሃኖች፣ በሁኔታዎችመሆኑ ቀጥሏል፡፡ 

በዚህም ሂደት አንድም ህይወታችን በሌሎች ይወሰናል፣ እንዲሁም ሌላ ተጨማሪ ማንነትን እንገነባለን፡፡ 

በዚህ የትውልድ ቅብብሎሽ ሂደት የሆነው ሁሉ ሆኖ ዛሬ ላይ ያለሁትን ማንነት ሆኘ አገኘሁት ታዲያ ይህ ማንነት የተሳሳት ይሁን ትክክለኛ እንዴት አውቃለሁመልሱ ቀላል እና ግልጽ ነው፡፡ 

ማድረግ ያለብህ ነገር ቢኖር በእያንዳንዱ የህወት ዘርፎችህ (በቤተሰብህ፣ በጤናህ፣ በግንኙነትህ፣ በገቢህ፣ በመንፈሳዊነትህ፣ በትምህርትህ፣ በስራህ …) ያለህን ውጤት ተመልከት፡፡ 

በውጤቶቹ ደስተኛ ነህ? ከሆንክ በተነፃፃሪ ቢሆንም ትክክለኛ ማንነት አለህ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም የህይወት ዘርፎችህ ውጤቶች የማንነትህ ውጤቶች ናቸውና፡፡ ካልሆነ ደግሞ ትክክለኛ ማንነትን አልተቀበልክም መለት ነው፡፡

ትክክለኛ ያልሆነ ማንነትን መቀበሌን ባውቅስ ምን ላደርግ እችላለሁ? 

ታዲያ መቸ እና እንዴት ይሆን የራሳችንን የህይወት ምርጫ እና ውሳኔ በራሳችን የምመርጠው?

በዚህ ሁኔታስ እኛ እየኖርን ያለነው በእውኑ የእኛን ህይወት ወይስ የሌሎችን?

የሌሎችን ከሆነስ መቸ ይሆን የራሳችንን ህይወት መኖር የምንጀምረው? እንዴትስ ይሆን የራሳችንን ህይወት መኖር የምንችለው?

ስለምን ቆም ብለን የህይወት ምርጫ እና ውሳኒያችንን ማን እና እንዴት እየመረጠልን እና እየወሰነልን እንደሆነ ልብ ማለት ተሳነን?

ከላይ የተነሱትን ጥያቄዎች መልስ በዋናነት ለአንባቢያን ትቻለሁ፡፡ 

ምናልባት በሂደት እንዴት የራሳችንን ህይወት በምንፈልገው አቅጣጫ መውሰድ እንደምንችል ፍንጭ ሊሰጥህ የሚችል ከዚህ በፊት በዚህ ድህረ-ገጽ የእረፍት ወይም ትርፍ ጊዜን መጠቀም አሁንኑ ተጫንና በጥንቃቄ አንብበው::

 ማጠቃለያ

@ ገና ከጨቅላነቴ ወላጆቸ ማንነታቸውን ወደ እኛ ከተቡ፡፡
@ በመቀጠልም የት/ቤት በመምህራን እና ሰራተኞች ማንነታቸውን ወደ እኛ አስተጋቡ፡፡
@ ዛሬም ትልቅ ሳለሁ ሌሎች ማንነታቸውን ወደ ማስተጋባት ቀጠሉ፡፡
@ ለመሆኑ በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ያለፍን እና አሁንም በእንዲሁ ያለን እኛ ማነን?
@ ራሳችንን በመገምገም እኛ የምንለው አዲስ ማንነታችንን እንገንባ::
@ ሃሳቤ ሃሳባችሁ የሆነ እስኪ ንገሩኝ …

አንዴ ቆም ብለህ አስብ፡-

o ዛሬ አሁንኑ ልትተገብረው የምትችለው ከዚህ ጽሁፍ የተማርከው አንድሁለትሶስትወዘተ ሃሳብ ምንድን ነው? 

o ስላንድ ነገር ብዙ መረጃ መኖር ዕውቀት ነው፤ መረጃውን በተግባር መጠቀም ደግሞ ጥበብ ነው እና አሁንኑ በተግባር ግባ!

 

አስተያየት፣ ተጨማሪ ሃሳብ እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁ በዚሁ ድህረ-ገጽ ፃፉልን!