መነሻ ሃሳብ

በማንበብ ህይወትን መቀየር ማንበብ ለምንችል ለሁላችንም በነፃ ያለ ምንም ክፍያ ያለን ትልቁ ሃብታችን ነው፡፡ ይሁን እንጅ ብዙዎቻችን ካለን ብዙ ሃብት ይልቅ የሌለን ላይ ስለምናተኩር አይታየንም፡፡ በመሆኑም አንብበን ራሳችን የመቀየር ሃሳብ አይታየንም፡፡ ካነበብንም የተሰማራንበትን የስራ መስክ የየቀን ድርጊት ለመከወን ከምናነበው የዘለለ አናነብም፡፡ ይሁን እንጅ አንድ በማንበብ ህይወቴን እቀይራለሁ ብሎ ለተነሳ ሰው አንብቦ ህይወትን እንደመቀየር አስተማማኝ መንገድ የለም፡፡ ለዚህም ነው ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ሲሉ በማንበብ ራሳቸውን ቀየሩ ሰዎች የሚናገሩት፡፡

መጽሐፍት ስናነብ አውቅነውም ሆነ ሳናውቀው ህይወትን የምናይበት መንገድ፣ አመለካከታችን፣ ድርጊቶቻችን እና ባጠቃላይም የምንኖረው ህይወት የመጽሐፉን ደራሲ ይሆናል፡፡  በዚህ የድህረ-ገጽ ጽሁፍ አጋጣሚ በሚመስል ግን ባይደለ ሁኔታ ስለተገናኘን እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ አንተ የምር የምትፈልግ ከሆነ ከዛሬ ጀምሮ አንብበህ ህይወትህን እንደምትቀይር እንነጋገር፡፡ በዚህም አንብበህ የመቀየር ሂደት እኔ የምችለውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ፈቃደኛ ነኝ፡፡

ማንበብ ልማድ ግንባታ

እንግዲህ እንደሚታወቀው እኛ ሰዎች ቀናችንን፣ ሳምንታችንን፣ ወራችንን ብሎም ዓመታችንን በሙሉ የምናሳልፈው አውቀን ወይም ሳናውቅ የገነባናቸውን ልማዶቻችንን በመከተል ነው፡፡ ይህንንም እውነታ ለመረዳት ምንም መጽሐፍ ማንበብ አይጠበቅብህም፡፡ ይልቁንም አንድ አፍታ ቆም በል እና በጣም በአብዛኛው ቀኖችህን እንዴት እንደምትጀምራቸው እና እንደምትጨርሳቸው ልብ ብለህ ተመልከት፡፡ በቀን ውሎህ የምታደርጋቸውን ክንውኖች ልብ ብለህ ብትመለከታቸው በጣም በአብዛኛው ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ህም ክንውኖች ከመደጋገማቸው የተነሳ ልማድ ሆነው ህወትህን የሚቆጣጠሩ ድርጊቶች ናቸው፡፡

በጣም አሳዛኙ ነገር ግን እንደ እኔ ከሆንክ ከዚህ የቀን ተቀን ውሎህ ብዙ ክንውኖች ውስጥ ህይወትን ለመቀየር የታሰበበት የንባብበ ጊዜ አለመኖሩ ነው፡፡ ልብ በል ይህን ስልህ ያንተን ችግር ነቅሸ በማውጣት በራስህ እንድታዝን እንድትጸጸት አይደለም፡፡ በራስህ ካዘንክ እና ከተጸጸክ  ሌላ ተጨማሪን ችግር ይዞ ይመጣል፡፡ ደግሞም ብቻህን አይደለህም፣ ይህ በጣም የብዙዎቻችን የህይወት እውነታ ነውና ይሁን፡፡

ዋናው ቁም ነገር ግን አሁን በዚህ አጋጣሚ ልክ እንደ ማንቂያ ደወል አንብቦ ወትን የመቀየር ሃሳብ የሚያወራ ጽሁፍ ስላገኘህ ደስስስ ይበልህ፡፡  ነገራችን ላይ ስለለህ ትንሽም ትሁን ትልቅ መልካም ነገር ሁሉ ደስስስ ሊልህ ይገባል፡፡ ደግሞም አንብቦ ህይወትን መቀየር ነፃ ስጦታ ትልቅ ሃብት ነው፡፡ አንተ ማንበብ በመቻልህ ይሄው ይህንን አንብቦ ህይወትን የመቀየር ድል አገኘህ፡፡ ያንተ አቻያዎች ወይም ትልቆችህ ማንበብ ቢችሉ ግን ምን ያህል እንደሚደሰቱ የሚመኙ ብዙዎች ናቸው፡፡  

እንግዲህ እስካሁን ባለው የቀን ተቀን ክንውኖችህ ምንም እንኳ ህወትህን ለመቀየር የታቀደ የማንበብ ልምድ ባይኖርህ እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ በጊዜው እና በሰዓቱ ውብ አድርጎ ሰራው እንዲሉ አንተ የምር አንብበህ ህይወትህን መቀየር ከፈለክ ይሄው ከዛሬ ጀምሮ ዕድሉ በመዳፍህ ላይ ነው፡፡ በጣም ደስ የሚ ዜና ደግሞ ከውስጡ ከፈለገ ማንም ሰው ጠንካራ የማንበብ ልማድ መገንባት እና ህወቱን መቀየር መቻሉ ነው:: አይደለም የማንበብ ልማድ ቀርቶ የመስረቅ፣ የመጠጣት፣ የማጨስ ልማድ እንኳን መገንባት ችሎ ስንቱ በየቀኑ እየተጃጃለ አይደል፡፡ ስለዚህ አንተ ደግሞ መደበኛ የሆነ እና ህይወትህን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቀይር የማንበብ ልማድ ማዳበር ትችላለህ፡፡

ላለማንበባችን የምናቀርባቸው የተለመዱ ምክንቶች

ውድ አንባቢየ አንብበህ ህወትህን ቀይር ስልህ አንተ የማንበብ ልማድ እና ፍላጎት እንደሌህ፣ በጣም ባተሌ እና ብዙ ስራ የሚበዛብህ እና የማንበቢያ ጊዜም  እንደሌህ፣ ዕድሜህ እንደገፋ እና መልፋት እንደሌለብህ አሊያም የስራህ ጸባይ እና የስራ ቦታህ ለማንበብ እንደማይመችህ እንደምትነግረኝ እገምታለሁ፡፡ ለእኔም በወቅቱ ከእነዚህ ጥቂቶቹ የእኔ ምክንያቶች ስለነበሩ አውቀዋለሁ፡፡ በነገርህ ላይ ምንም ያህል ስራ እንስራ፣ ምንም ያህል ዕድሜ ላይ እንሁን፣ ምንም ያህል ባተሌ እንሁን የመጨረሻ የህይወታችን ግብ እኮ ጤነኛ እና ደስተኛ ህይወትን መኖር መቻል ነው፡፡ ይህንን ያላተረፍንበት ህይወት ለምናችን ነው?

ያም ሆነ ይህ አሁን ባለንበት ማንኛውም ተጨባጭ የህይወት ሁኔታ ላይ ሆነን ማድረግ እንደምንችል ልሞግትህ ነው፡፡ እናም ላለማድረግህ ማስረጃ የሚሆኑ ትክክል የሚመስሉህን ምክንቶች ከመደርደር በመቆጠብ ልብ ብለህ አዳምጠኝ፡፡ መግባባት ላይ እንደምንደርስ እና ከዘሬ ከዚች ቅጽበት ጀምሮ በማንበብ ራስህን ለመቀየር በመወሰን እና በመጀመር አስቸጋሪ ሁኔታ ሲገጥምህ ሲደክመኝ አላርፍም በማለት እውን እንደምታደርገው ተስፋ አለኝ፡፡ ራስህን ቀይረህም ይህንን ጽሁፍ ያነበብክበትን ቀን እና አጋጣሚ ከማረሱ ቀኖች አንዱ እንደምታደርገው እና እንደምትደውልልን ወይም በኢሜል እንደትጽፍልኝ አልጠራጠርም፡፡ 

አንብበህ ራስህን የመቀየርን ሂደት ግልጽ ለማድረግ ጥቄዎች ልጤቅህ፡፡ ተኝተህ አድረህ ጠዋት ከእንቅልፍህ በስብት ሰኣት ነው የምትነሳው? ቀኑን ሙሉ ስትሰራ አድረህስ በስንት ሰዓት ነው የምትተኛው? በቀን ሙሉ ውሎህስ ምን ህሉን ሰዓታት ይህ ነው ብለህ ላልመደብክለት ተግባር ታጠፋለህ? እንግዲህ ውድ አንባቢየ ከላይ ለተነሱት ጥያቄዎች እኔ መልስ አልሰጥህም፡፡ መልሱን አንተ እና አንተ ብቻ ነህ የምታውቀው፡፡

ጊዜ እጥረት እና ምንባብ

እንግዲህ የብዙዎቻችን በመደበኛ መልኩ ያለማንበባችን የመጀመሪ ምክንያታችን የጊዜ እጥረት ነው፡፡ ዳሩ ግን ከእኔ እና ካንተ የበለጠ ባተሌ የሆኑ እና ዓለም ላይ ተጽዕኖ ያመጡ እንደ እነ ቢል ጌት፣ ኢሎን ማስክ, በርናርድ አርናውልትየመሳሰሉትን ሰዎች ህይወት ብትመለከት ዛሬውኑም ሳይቀር በቀን በምንም መንገድ የማይደራደሩበት የማንበቢ ጊዜ አላቸው፡፡ ስለዚህ በእውኑ አንተ እና እኔ ከእነዚህ ሰዎች በለጠ ጊዜ አትሮን ነው የማንበቢ ጊዜ የለኝም የምንለው? ምን እየሰራን ቢሆንስ ነው ጊዜ ያጠረን? ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ስለምን ዘወትር ከእንቅልፋችን ከምንነሳበት ወይም ከምንተኛበት ሰዓት ቢያንስ 15 ደቂቃ ቀደም ወይም ዘግየት ብለን በመነሳት ወይም በመተኛት ከ10-15 ደቂቃ ያህል በየቀኑ ብናነብስ? እናስብበት፡፡

በእድሜ መግፋት እና ምንባብ

ደግሞም ዕድሜየ ገፍቷል ከዚህ በኋላ አነበብኩ አላነበብኩ ምን የት ለመድረስ ነው ካልክ የሜሪ ወከርን 116 ዓመቷ ማበብን የተማረች ሴት ታሪክ አንብብ፡፡ ልብ በል ለመማር ዕድሜ አይገድብም፡፡ እንዲውም ልብ ብለኸው ከሆነ በአብዛናው ባልተጠበቀ ዕድሜ ላይ  ሰዎች በህይወታቸው አንብበው ሲቀየሩ በቀላሉ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ስለሚተርፉ በዚህ ዲጊታል ዘመን በብዙ ሰዎች ተቀባይነት ማግነት ደግሞ ምን ያህል ሊጠቅምህ እንደሚችል ይገባሃል ብየ አስባለሁ እና ዕድሜህን አንብበህ ላለመቀየር ለቅጽበትም ምክንያት አታድርግ፡፡

እንግዲህ ውድ አንባቢየ በዚህ ጽሁፍ ምንባብ እስካሁን በነበረን ቆይታ በመደበኛነት በማንበብ ህወትህን መቀየር እንደምትችል ያመንክ እና ፍንጭ ያገነህ መስለናል፡፡ ይሁን እንጅ በዚህ ጽሁፍ ትኩረት የተደረገው በቅድሚ እነዲህ እንደምታደርግ ፍንጭ መስጠት እና ማሳመን ነበር፡፡ ሆኖም በሃሳቡ ተስማምተህ ሳለ ወደ ተግባር ልትገባ ስትሞክር እንዴት መደበኛ የማንበብ ልማድ እንደምትገነባ በግልጽ የተባለ ነገር የለም፡፡ ስለዚህ በተነሳው ነጥብ ላይ ፍንጭ ካገኘህ እና ካመንክበት በሚከተለው የድህረ-ገጽ ጽሁፍ ላይ ግልጽ የሆነ መደበኛ የማንበብ ልማድ ግንባታን ሂደት ያሳይሃል እና ሊንኩን በመጫን መደበኛ የንባብ ልማድ ግንባታ የሚለውን ጽሁፍ በጥንቃቄ አንብብ፡፡ ጽሁፉን በጥሞና ስላነበብከው ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

አንዴ ቆም ብለህ አስብ፡-

ዛሬ አሁንኑ ልትተገብረው የምትችለው ከዚህ ጽሁፍ የተማርከው አንድ … ሁለት … ሶስት … ወዘተ ሃሳብ ምንድን ነው?  

ስላንድ ነገር ብዙ መረጃ መኖር ዕውቀት ነው፤ መረጃውን በተግባር መጠቀም ደግሞ ጥበብ ነው እና አሁንኑ ወደ ተግባር ግባ!

 

አስተያየት፣ ተጨማሪ ሃሳብ እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁ በዚሁ ድህረ-ገጽ ፃፉልን!