መግቢያ

ዙዎቻችን የማናውቀው እጅግ ድንቅ ስኬታማ መሆን ያለበትን ይሆን ዘንድ ልፈቀድንለት አንድ ድንቅ ማንነት በውስጣችን አለ፡፡ ይህንን በውስጣችን ያለ የተኛ ማንነት ራሱን እንዲሆን ብንፈቅድለት እና ብንኖረው የእኛን ህይወት ብቻ ሳይሆን የዓለምን ገጽታ የሚለውጥ እጅግ ድንቅ ማንነት ነው፡፡ ይህንንም ያላወቅነውን እና ያልኖርነውን ማንነት ያልተኖረ ማንነት ብየዋለሁ፡፡ ስለሆነም መሆን፣ ማግኘት እና መስራት የምንፈልገው እጅግ በጣም ትልቅ ነገርም ቢሆን ካለ ያንን የሚያሳካው ድንቅ ማንነት በውስጣችን ነው፡፡ ወደ ውስጣችን እጅግ በጥልቅ እንቆፍር ማለትም ራሳችንን ጠንቅቀን እንወቅ፡፡

የሳይንስ እና የመንፈሳዊው ዓለም ስለሰው ችሎታ ምን ይላል?

በአጠቃላይ ሰውን ስንመለከት በቅዱስ መጽሐፍ ለሚያምን ሁሉ ያቻለዋል ይላል፡፡ በሳይንሱ ደግሞ በውስጥህ ያሰብከውን እና ያመንከውን ማንኛውንም ነገር ትሆናለህ ይላል፡፡ የሳይንሱ እና የመንፈሳዊው ዓለም ሁለቱም በሰው ልጅ ችሎታ ይስማማሉ፡፡ ነገር ግን በአብዛኛው የሳይንሱ ዓለም ያሰብከው እና ያመንከው ነገር ሁሉ በራስህ መሆን ትችላህ ይላል፡፡ የመንፈሳዊው ዓለም ደግሞ በእግዚአብሔር ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል ይላል፡፡ ራሳችንን መፍጠር ጨምሮ የሁሉ ባለቤት እርሱ ነው፡፡ ማንም ሰው ፈልጎ እና አቅዶ አልተፈጠርም፡፡ በመሆኑም አንዳች ነገር እንኳን ከሰው እና በሰው የሆነ እና የሚሆንም ነገር የለም፡፡ በመሆኑም የመንፈሳዊውን ስለሰው ልጅ ችሎታ የተገለጸውን ጽንሰ-ሃሳብ ሙሉ በሙሉ አምናለሁ፡፡ በእግዚአብሔር ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል የሚለው አምላካዊ ጽንሰ-ሃሳብ ለሁላችንም የሰው ልጆች እኩል የሚሰራ ከአምላክ በነፃ የተሰጠን መልካም ስጦታችን ነውና ልብ እንበል፡፡  

በችሎታህ ትጠራጠራለህን?

ብዙዎቻችን በእግዚአብሔር ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል የሚለውን አምላካዊ ጽንሰ-ሃሳብ ለመንፈሳዊ ሰች ብቻ የሚሰራ አሊያም እንዲሁ ነገር ለማድመቅ የተባለ ይመስለናል፡፡ ነገር ግን ይህ ጽንሰ-ሃሳብ እውነትነቱ ማስረጃ ካሻን ከቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የተጠቀሱ የዓለም ህዝብ ለማመን የተቸገረባቸው ነገር ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት ድንቅ ድንቅ ስራዎችን (ገድል እና ታምራትን) የሰሩ ቅዱሳን ነቢያትን፣ ሐዋርያትን፣ መነኩሳትን እና ሌሎች ሰዎችን ታሪክ ማንበብ እና መረዳት እንችላለን፡፡ ይህም እንዲሁ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተፃፈ ታሪክ መስሎ ከታየን በእግዚአብሔር ራሳችን ላይ ስለሚደረጉ ድንቅ ነገሮች እናስተውል፡፡ ዛሬም ቢሆን ዓለምን አጀብ የሚያሰኝ ድንቅ ስራ እየሰሩ ያሉትን ጥቂት ሰዎች የህይወት ታሪክ ብናጠና እምነታችንን እናዳብራለን፡፡

አሳዛኙ ነገር ግን በአምላካችን ባለን እምነት ልክ የፈለግነውን የመሆን እና የመስራት ችሎታ ከአምላካችን የተሰጠን ነፃ ጸጋ ሳለን እኔ በተፈጥሮየ ደካ ነኝ፣ ቁጡ ነኝ፣ አልችልም፣ ትምህርት አይሆነኝም … ወዘተረፈ እያልን የተሰጠንን ጸጋ እና ህይወታችንን ጭምር እናባክናለን፡፡ 

እኔ በበኩሌ በእግዚአብሔር ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል የሚለውን አምላካዊ ጽንሰ-ሃሳብ ከተረዳውሁ ዕለት ጀምሮ ሰውን ልጅ ራሴን ጨምሮ በተለየ መንገድ ማየት እና መረዳት ጀመሪያለሁና አናንተም አስቡበት፡፡ ራሴንን ባለመረዳት ያልኖርኩትን ማንነቴን ያልተኖረ ማንነት ብየዋለሁ፡፡ 


አንዴ ቆም ብለህ አስብ፡-

ዛሬ አሁንኑ ልትተገብረው የምትችለው ከዚህ ጽሁፍ የተማርከው አንድ … ሁለት … ሶስት … ወዘተ ሃሳብ ምንድን ነው?  

ስላንድ ነገር ብዙ መረጃ መኖር ዕውቀት ነው፤ መረጃውን በተግባር መጠቀም ደግሞ ጥበብ ነው እና አሁንኑ ወደ ተግባር ግባ!

በጽሁፉ ላይ ተጨማሪ ሃሳብ፣ አስተያየት፣ ጥያቄ ካለ መነጋገር መርሃችን ነው፡፡

ጽሁፉ ይጠቅማል ብለው ካሰቡ ለሌሎች ያጋሩ፡፡