መነሻ ሃሳብ
ጭቅጭቅ በሚበዛበት ቤት ውስጥ ለሚኖሩ ህጻናት ብቻ ሳይሆን ለእኛም ለታላላቆች ሳይቀር ጭቅጭቅ የተለመደ የህይወት ክፍል ይሆናል። ነገሮችም የሚፈጸሙት በጭቅጭቅ መሆኑን ሳናውቅ እንዲሁም ወደን ሳይሆን ተገደን በድብቁ አእምሯችን እናምናለን፡፡ በራሳችን ህይወትም በተግባር እናደረገዋለን፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ የተደጋገመለትን የሚጠቅመውንም ይሁን የማይጠቅመውን ነገር እንደ እውነት አድርጎ መቀበል ብቻ ሳይሆን በተግባርም ሊያደርገው ይገደዳልና፡፡ ይህ ለብዙ ሰው የቅንጦት አና የወግ ማጥበቅ ሃሳብ ወይም የጥናት መረጃ ይመስለዋል፡፡ ይሁን እንጅ ይህ የአእምሮ አሰራር አመለካከታችንን በመወሰን የዕለት ተዕለት ህይወታችንን የሚወስንና የማያሻማ እውነታ ነው::
ይህም እውነት መሆኑን ለመረዳት
በሲጋራ እና በተለያዩ የጤና ጠንቅ ሱስ የተጠመዱ ሰዎችን ህይወት መመልከት በቂ ነው፡፡ እኒህ ሱሰኞች እንደሚታወቀው ይህንን ሱስ
ሲጀምሩት በመጀመሪያ እንደ መዝናኛ እና ሲፈልጉ እንደሚያቆሙት ሆነው ነው፡፡ ነገር ግን ከተወሰነ ድግግሞሽ በኋላ (ከ21 ቀናት
በኋላ) አይደለም ከናካቴው ማቆም ቀርቶ ሰዓት እንኳን ማዛነፍ የማይችሉበት በረጃ ይደርሳሉ፡፡ ሳንባ እና ልዩ ልዩ ወሳኝ የአካል
ክፍላቸው ከጥቅም ውጭ ሊሆን ወራት፣ ሳምንታት፣ ቀናት እንደቀራቸው በሃኪም ተነግሯቸው እንኳን ከማጨስ አያቆሙም፡፡
ይህ ምንን ያመለክተናል?
ሲጋራ
ሱስ የሚያስይዝ ንጥረ-ነገር ስላለው ነው እንደምትሉ አሰብኩ፡፡ እውነታው ግን አእምሮ (ድብቁ አእምሮ) የተደጋገመለትን ማንኛውም
ነገር ያለምንም ማዳላት እንደእውነት በመቁጠር ለተግባር ሌት ተቀን እንድንታመን ያደርጋል፡፡ ይህ እና መሰል ክፉ ልማዶች (ጭቅጭቅ)
ደግሞ ከተደጋገመ ከአዋቂዎች እጅግ የበለጠ በህጻናት ላይ ውጤታማ (እጅግ አስከፊ) ነው፡፡ ምክንያቱም ህፃናት (እስከ 8 ዓመታቸው)
በአብዛኛው ንቁ አእምሯቸው ሳይሆን ድብቁ አእምሯቸው ነው አገልግሎት የሚሰጠውና፡፡
ሌላው እጅግ በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ፡-
የሰዎች አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ሀሳብ ባካባቢው ያለውን ሰው አእምሮ፣ ሃሳብ፣ ስሜት እና አካል ብቻ ሳይሆን የውሃን መደበኛ ስሪተ ቅርጽ ሳይቀር በአዎንታዊ እና በአሉታዊ መልኩ በከፍተኛ ሁኔታ ተጽኖ ያደርሳል፡፡ ይህም ማለት በአንድ ቤት ውስጥ በጭቅጭቅ ጊዜ አንድ አሉታዊ ንግግርን የሚያደርግ ሰው ቢኖር ይህ ሰው በቤት ውስጥ ያሉ ሌሎች ሰዎችን አሉታዊ ሃሳብና ስሜት እንዲያስቡ እና እንዲሰማቸው ማድረግ ብቻ ሳይሆን የውሃን መደበኛ የሚያምር ስሪተ ቅርጽንም እንኳ በጣም ወደ ሚያስጠላ ቅርጽ እና ቅርጻልባነት ይቀይራል፡፡ ይህንን በተመለከተ ለበለጠ ግነዛቤ የጥናት ውጤቶችን ማንበብ እና የዘርፉ ባለሙያዎችን ንግግር ማዳመጥ ይቻላል፡፡
ነገር ግን ብዙዎቻችን ወላጆች አይደለም ይህ አሉታዊ ሃሳብ (ጭቅጭቅ) ልጆቻችንን በዚህ ደረጃ ይጎዳቸዋል ብለን ልንጠነቀቅ ቀርቶ ልጆቻችንን ሆነ ብለን በአካል ስንቀጣቸው እና ከህሊናቸው በላይ የሆነ ስድብን ስንሰድባቸው እንኳን በጣም በኩራት እና ልጆችን ወደ ተሻለ ማንነት እያስተካከልናቸው እንደሆነ በመተማመን ነው፡፡
ስለሆነም ውድ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች እና ተንከባካቢዎች ከላይ የቀረቡት መረጃዎች ምን ያህል ስለልጆቻችን መጠንቀቅ እንዳለብን በግልጽ የሚያሳዩ እና አሁን እያየነው ያለነው የትውልድ የህይወት መንሻፈፍ የራሱን ድርሻ እንደሚወስድ እንደተረዳችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ከላይ ያለው መረጃ እንዳለ ሆኖ ደስ የሚለው ነገር ግን በውይይት እና ምክክር በሰፈነበት ቤት ለምንኖር ህጻናት ብቻ ሳይሆን ለእኛም ለታላላቆች ሳይቀር እንዲሁ ነው፡፡ ማለትም በውይይት እና ምክክር የተለመደ እና ነገሮችም የሚፈጸሙት በውይይት እና ምክክር መሆኑን በውስጣቸን እናምናለን፡፡
የተግባር ሃሳቦች፡-
ስለሆነም
ውድ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች እና ተንከባካቢዎች ለራሳችንም ሆነ ለልጆቻችን የተሻለ ህይወት ስንል በቤታችን ውስጥ መተሳሰብ እና መተዛዘን
እንዲሁም አስፈላጊ ሲሆንም ውይይት እና ምክክርን ልማዳችን ልናደርግ ይገባል እላለሁ፡፡
መጨቃጨቅን ለምደነው እንደምናደርገው ሁሉ መተሳሰብ እና መተዛዘንን እንዲሁም ውይይት እና ምክክርን መልመድ እና መኖር እንችላለን፡፡ ዋናው ልብ ብሎ በማሰብ መልመዱ ነው::
2 አስተያየቶች
ትክክል ሃሳብ ነው። በጭቅጭቅ ውስጥ ያላደገ ሰው በተለምዶ ሰምታችሁ ከሆን ከ 2 ደቂቃ በላይመሰማትም ሆነ መናገር ኣልችልም ይላሉ ምክንያቱም በዕድገቱ ውስጥ ኣለተደጋገመበትም ወይንም በድግግሞሸ ጠባይ ኣልተያዘም ።
ምላሽ ይስጡሰርዝስለተጨማሪ ሃሳባዎ እጅግ በጣም እናመሰግናለን!
ምላሽ ይስጡሰርዝ